በቾክ እጥረት ትምህርት ቤቶች ስራ እያቆሙ ነው ተባለ

January 24, 2019

በአማራ ክልል ማእከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በቾክ እጥረት ስራ እያቆሙ መሆኑን ትላንት ለንባብ የበቃው በረራ ጋዜጣ ዘገበ፡፡ እንደጋዜጣው ዘገባ

https://www.youtube.com/watch?v=pJpzsue5H3c&t=917s

በወረዳው ጫራ ሰቀላ ቀበሌ የሚገኝ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በጀት ስላልተለቀቀ ከጥር 15 ቀን 2011 ጀምሮ ስራ ማቆሙን የትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህር አቶ ጌታቸው ማንደፍሮ በፊርማቸው በወጣ ደብዳቤ ገልፀዋል፡፡ ‹‹የትምህርት ቤቱ በጀት በመታገዱ ነው ››በሚል ምክንያት በተሰጠበት ችግር ቾክ(ጠመኔ) እና መሰል የትምህርት መሳሪያዎች እጦት የተነሳ መምህራን ክፍል ገብተው ማስተማር ባለመቻላቸው ትምህርት ቤቱ ስራ ማቆሙንም ጋዜጣው ዘግቧል፡፡ በወረዳው ሌላ ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ መምህር ለበረራ እንደገለፁት ለትምህርት ቤቶቹ የሚሰጠው በጀት በተለያየ መንገድስለሚታገድ ከጫራ ሰቀላ ትምህርት ቤት በተጨማሪ ሌሎች ትምህርት ቤቶችም ስራ እያቆሙ ይገኛሉ፡፡ በተለይ ከወረዳው ከተማ በርቀት የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የማስተማሪያ ቁሳቁሶች ስለማይሟሉ የባሰ ችግር እየገጠማቸው መሆኑም ተነግሯል፡፡ የወረዳው ገንዘብና ኢኮኖሚ ፅህፈት ቤት የትምህርት ቤቱን በጀት እንደሚይዝባቸው ለበረራ የገለፁት መምህራን በዚህ ምክንያት ለማስተማር መቸገራቸውን አስረድተዋል፡፡ የወረዳው ገንዘብና ኢኮኖሚ ፅህፈት ቤት ስለጉዳዩ ተጠይቆ ትምህርት ቤቶቹ ገንዘብ ለማወራረድ ህጋዊ ሰነድ ካላቀረቡ በጀት ሊያዝባቸው እንደሚችል ጠቁሞ በማስተማሪያ ቁሳቁሶች እጦት ስራ ያቆሙ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን እንደማያውቅ ተናግሯል፡፡

Previous Story

አዴፓ ከዳተኝነት፣ ከለዘብተኝነትና  ከይሉኝታ ፖለቲካ ወጥቼ በቁርጠኝነት የህዝባችንን ጥቅም ለማረጋገጥ እየተንቀሳቀስኩ መሆኑ ይታወቅልኝ አለ

Next Story

በባሌ ሀገረ ስብከት ሮቤ ከተማና አካባቢው የተቃጠለው ቤተክርስቲያን ጉዳይ…

Go toTop