ኦነግ ሸኔ አዲስ ያሰለጠነውን የጦር ሰራዊት ያስመረቀ ሲሆን በኦሮሚያ የሰሜኑ ክልል ድል እየቀናኝ ነው አለ (የመረጃ ቪዲዮ)

July 19, 2022

በወለጋ ውስጥ እንዲሁም በጉጂና በሰሜን ኦሮሚያ አማራ አዋሳኝ አከባቢዎች ሰራዊቱን አሰማርቶ ከመንግስት ሃይሎች ጋር ውጊያ የገጠመው ይህ ታጣቂ ቡድን በተለያዩ ጊዚያት ያሰለጠናቸውን ታጣቂዎቹን በማሰማራት ከፍተኛ የሆነ ውድመት እና ግድያ እየፈፀመ መሆኑ ይታወቃል።

ያሰለጠናቸውን ታጣቂዎቹን በስፋት ጦርነት ባለባቸው የከሚሴና አጣዬ እከባቢዎች እንዲሁም በወለጋ እንደሚያሰማራ ከድርጅቱ ኮሚኒኬ የተነበበ መረጃ ይጠቁማል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሜን ኦሮሚያ በኦነግ ታጣቂ ሃይሎች እና በመንግስት የትሰጥታ ሃይሎች መካከል ከባድ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑ ታውቁል፡

የደረሰን ቪዲዮ እንደሚያሳየው በሰሜን ኦሮሚያ አማራ አዋሳኝ አከባቢዎች ላይ በከባድ መሳሪያ የተደገፈ ጦርነት አየተካሄደ ነው ፡ የኦንግ ሰራዊት እባላት በተለያዩ ወረዳዎችና የመንግስትን ንብረት በማውደም እና ሰዎችን በመግደል ላይ መሆናቸው ተነግሩአል።

መረጃ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ በሚኖሶታ የሚያዘጋጀው የኢትዮጵያ ቀን ጁላይ 23 ይከበራል – ሲራክ ህይሉ

Next Story

“አማራ ማስተዋል ጀምሯል። አማራው በአማራነቱ እንዳይደራጅ የሸፈነውን ኢትዮጵያዊነት ግርዶሽ ቀዳዶታል” – መስከረም አበራ

Go toTop