ጦርነቱን በእነ ሲኤንኤን፣ ቢቢሲና ሌሎች የምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን የፈጠራ ወሬ እናሸንፋለን ብለው ተስፋ የሰነቁ ካሉ አሸባሪው ሕወሓት ድል ያደርጋል ብለው ዘላለም ሲጠብቁ ይኑሩ ሲሉ ኬንያዊው ፖለቲከኛ ፋራህ ማሊም ገለፁ።
የኬንያ ብሔራዊ ጉባኤ የቀድሞው ምክትል አፈ ጉባኤ እና የፓርላማ አባል ፋራህ ማሊም ሙሃመድ የሽብር ቡድኑ ሕወሓት ንፁሃንን እያጠቃ ወደ አጎራባች ክልሎች በገባ ቁጥር እየተከበበና ተጠርጎ የሚወገድበትን ሁኔታ እየፈጠረ ነው ብለዋል።
አዲስ አበባ እገባለሁ ብሎ የፎከረውና ከመደበቂያ ዋሻው የራቀው የሽብር ቡድኑ በፈፀመው ስህተት ራሱን እያጠፋ እንደሆነም ጠቁመዋል።