ነፃ አስተያየቶች - Page 87

የባለሙያ ቡድናችን ከፍተኛ ደረጃ ያላቸውን የግልነፃ የመረጃ ስብሰባዎች

ጉርንቧቸውን ሲያንቋቸው ፋኖ ድረስ ትንፋሽ ሲያገኑ ፋኖ ፍረስ! -በላይነህ አባተ

January 14, 2022
ታሪክ እንደሚያስረዳውና እንደምናውቀው ፋኖ አገር ስትወረር፣ የሕዝብ ኑሮና ሰላም ሲናጋ እንደ አንበሳ አግስቶ ጠላትን የሚመክትና የሚያንበረክክ እምቅ ኃይል ነው፡፡ ለሺህ ዘመናት ፋኖ ኢትዮጵያን የወረረውን

ህወሀት ኢትዮጵያን እንዲዘረፍ መንገድ የከፈተው ህገ መንግስት! – በሰዋለ በለው

January 13, 2022
የአንቀጽ 39 ቅጥያዎች (ተቀጽላዎች) ህወሓት “የኢትዮጵያ ያለውን ዘር-ተኮር-ሕገ መንግሥት” እ. አ. አ. በ1994 ዓ.ም ባካሄደው የፓርላማ ምክር ቤት ውሳኔ ያስፀደቀውን ሕገ መንግሥት ማግኘት ሲችል፣

”ተቃዋሚ ፓለቲከኞች” ከተቃውሞው  መግለጫው በኋላስ? – ፊልጶስ

January 13, 2022
እንደመግቢያ፥ ይብላኝ ለአንች!— ቦርቀሽ ሳትጨርሽ ሩጠሽ – ሳትደርሽ ሳይጠናም – አጥንትሽ፤ ደምሽ – ለፈሰሰው የሴትነት ክብርሽ፣ በግፍ ለተቀማው፤ ገና በማለዳው፣ ቀኑ ለመሸብሽ ጠላቶችሽማ ገና

ውድ ወንድሞችና እህቶች – ሙሉጌታ በትረ ገብረማሪያም

January 12, 2022
እንደገና አብዝቶ በአያሌው ጤና ይሥጥልኝ!! እንዲያውም ብዙም … ወደ የቅርብ ሩቅ የኋለ መለስ ብለን …፣ ልክ በ“ወንጀለኛው ዳኛ” መጽሐፍ በጉልህ እንደተመለከተው ሁሉ፣ምናልባትም ”ከወዳጅ ጠላት ያድን“፣ ”ልዩ ዋጋ

ፍትሕን እራሳቸዉ አልከሰከሷት!-መኮንን ብሩ(ዶ/ር)

January 9, 2022
ከክርስቶስ ዉልደት አንድ መቶ ሰባ ዓመታት በኋላ የተወለደዉ ሮማዊዉ ዳኛ ዮፒያን “ፍትህ ማለት ሁሉም የድርሻዉን ይቀበል ዘንድ የሚያደርግ ሚዛን ነዉ” ሲል ይገልፃል። አርስጣጣሊስ በበኩሉ “የሰዉ ልጅ ከሕግ እና ፍትህ ዉጪ ከሁሉም አዉሬዎች የከፋ አደገኛ ፍጡር ነዉ” ሲል የሕግና ፍትህን አስፈላጊነት ያሰምርበታል። ያለ ሕግ እና ያለ ፍትህ ሀገር ሊኖር ቢችልም ሰላምና ዲሞክራሲ ግን ፈፅሞ አይታሰብም። እንግሊዛዊዉ ፈላስፋ እና ፖለቲከኛ ፍራንሲስ ቢከን “ፍትሕን መጠበቅ ያልቻለ ሕብረተሰብ ወይም ሀገር እራሱን መጠበቅ አይችልም” ሲል ፅፏል። ፍትህ ለሰዉ ልጆች በመከባበር አብሮ ለመኖር ወሳኝ ነዉ። ያለ ፍትህ ጭቆና ወይንም አምባገነን የትዉልድ ነቀርሳ ሆኖ ይንሰራፋል። “ፍትህ ባለበት ማንኛዉም እዉነት አይጎዳም” ይሉ ነበር ጋንዲ፤ ያለ ፍትህ ግን ሁሉም ይጎረብጣል። ከአንድ ቀን በፊት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ የእራሳቸዉን መንግስት በተለያየ ፈርጁ አምርረዉ ሲወቅሱ ተደምጠዋል። በተለይም የፍትህ ስርሃቱን የዘቀጠና የተጨመላለቀ ሲሉ ገልፀዉት ነበር። ይሁን እንጂ እስከ ገና ባዕል ምሽት ድረስ ጠቅላዩ ሊሉ የፈለጉት በትክክል የተገለፀለት ያለ አይመስለኝም። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት ለፍትህ የሚታገል ግን ፍትህን የተራበ ሕዝብ በመሆኑ የጠቅላዩን “የዘቀጠ የፍትህ ስርሃት” ንግግርን ያዳመጠዉ የነገን የፍትህ ዘመን ተስፋ በመናፈቅ እንጂ ሰዉዬዉ በኢፍታዊነት ቆስለዉ አመርቅዘዋል ብሎ አልነበረም።ይሁን እንጂ የሕመማቸዉ ዱብዳ በጌታ ልደት ምሽቱ ተገለጠ። በርካቶችን ለሞትና ለስቃይ የዳረጉትን ፋሺስቶች በቀጭን ትህዛዝ ከእስር እስኪለቁ ድረስ በእዉነትም አብዝተዉ የተጨማለቁ ብቻ ሳይሆን በኢፍታዊነት ነቀርሳ የቆሰሉና የሚያጣጥሩ በሽተኛ መሆናቸዉን ያልጠረጠሩ ሁሉ ዕጢ አስጣሉ። አዎን ጠቅላዩ በኢፍታዊነት በፀና ታመዋል። አመርቅዘዋልም። በአንድ ወቅት እራሳቸዉ ሲናገሩ “ከዉጪ ሀገራት ለምኜ ያመጣሁትን ፍራንክ ምንም ላደርገዉ እችላለሁ፤ …… ፓርላማዉም ሊጠይቀኝ አይገባም” ብለዉ ሲመፃደቁ ብዙዎቻችን ሰምተን እንዳልሰማ ያለፍነዉ ሰዉዬዉ በለመኑት ሳንቲም እየሰሩ ያሉት ለሀገር ሊጠቅሙ የሚችሉ ፓርኮችና መዝናኛ ቦታዎች በመሆናቸዉ እንጂ የመንግስት ስልጣን ላይ ተቀምጦ፣ በሕዝብ ጊዜና ገንዘብ ከሀገር ሀገር እየበረሩ፤ በትረ ስልጣኑንም ሆነ ማዕረጉን ተላብሰዉ በየሄዱበት ዕቅፍ አበባ እየታቀፉበት ልትጠይቁኝ አትችሉም የሚለዉ አባባላቸዉ ዉሃ የማይቋጥር ተላላ አባባል መሆኑ ሊገባቸዉ እንዲት እንዳልቻለ ተገርመን ትተነዋል። ምናልባት ያኔ የሕመማቸዉ ሁኔታ ቀላል ቁስል ቢጤ በመሆኑ እያደር ይደርቃል ያሉ በርካቶች ሳይሆኑ አይቀሩም። አሁን አሁን ግን ቁስሉ ዉስጥ ዉስጡን ሳያመረቅዝ የቀረ አይመስለኝም። ይህ ደግሞ አደገኛ ነዉ። አሜሪካዊዉ ገጣሚ እና ፀሐፊ ተዉኔት ጀምስ ባልድዊን እንደሚለዉ “አለማወቅ ከስልጣን ጋር ከተጣመረ በጣም አደገኛ ነዉ”። ጠቅላዩ የኢፍትሃዊነታቸዉን ጥልቀትና ንቅዘት አለማወቃቸዉ ከድርጊታቸዉ በላይ አደገኝነቱ አስፈርቶኛል። ማርክስ ኤንግልስ እና ሌኒን የሶሻሊዝም መገለጫዎች የሆኑትን ያህል ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ እና ደብረፂሆን የሽብርተኛዉ ትህነግ ማዕተሞች ናቸዉ።እነዚህ ፋሺስቶች  የሃያ ሰባቱ ዓመታት የኢትዮጵያዊያን ስቃይ እና እንግልት፣ ለብዙ ሺዎች ከሀገር መሰደድ፣ ለበርካቶች አካለ ስንኩል መሆን፣ ለመቶ ሺዎች ያለ ወላጅ አልያም ያለ ልጅ ባዶ መቅረት ተጠያቂ ናቸዉ። በተጨማሪም ላለፉት አንድና ሁለት ዓመት በተኙበት ለተረሸኑ፣ ከወላጆቻቸዉ ተመንጭቀዉ ተወስደዉ ለተደፈሩ፣ ቅዬቸዉ በትግራይ ወራሪዎች ተወሮ በቁማቸዉ ለተቃጠሉ ወገኖቻችንም ኃላፊነቱ በእነሱ ጫንቃ ላይ ነዉ። ታዲያ አንድ ቀን ለፍርድ ሳይቆሙና ሳይጠየቁ መለቀቃቸዉ የማያበሳጨዉ ካለ እሱ ገዳዩና ደፋሪዉን መሆን አለበት። ለዚህም ወንጀል ፍትህን የማይሻ እርሱ በሽተኛ ነዉ። ጊዜ ይፈጃል እንጂ ፍትህ ደግሞ ሁሉም ላይ መፋረዷ አይቀርም። ፍትህ ያጎደለም፣ ፍትህ ያዛባም ሁሉም በጊዜ ዉስጥ ዋጋዉን ከፍትህ ያገኛል። ከሁለት ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ የቀድሞ ነገስታትንና መሪዎችን በመጠቃቀስ የሚመስለኝን ፁሑፍ ለአንባቢዎቼ አቅርቤ ነበር። መይሳዉ ካሳን በጀግንነቱ፣ እምዬ ሚኒሊክን በብልሃተኝነታቸዉ፣ ኮረኔል መንግስቱን በሀገር ፍቅር ስሜታቸዉ፣ እንዲሁም ዶክተር አብይን ከፕሬዘዳንት ሊንከን ጋር በማመሳሰል ኢትዮጵያን በዚህ ወቅትም ለማስቀጠል መቻላቸዉን በመተረክ የእኛዉ ሊንከን ብያቸዉ ነበር። በዚያ ፁሑፌ አልፀፀትም፤ እንደዉም አሁንም ቢሆን ያ ዕምነት እና አመለካከት በእሳቸዉ ላይ አለኝ። ነገ ወይም ከነገ ወዲያ በሆነ መልኩ ብቅ ብለዉ የተዋጋሁት ለኢትዮጵያ አንድነት ስል አልነበረም እስኪሉ ድረስ (የሚሉ ከሆነ) እኔ ለኢትዮጵያ መዝመታቸዉን አደንቃለሁ። እቀበላለሁ። ይሁን እንጂ ይህን ያህል ጭፍን እና ኢፍትሃዊ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ መቼም ገምቼ አላዉቅም ነበር። ይህ ብቻ አይደለም፤ መዋሸትም እንደሚችሉ ታዝቢያለሁ፣ በመሆኑም ዳግም ላምናቸዉ እቸገራለሁ። “ሽማግሌ ከፍርድ በፊት አትላኩ እኔ ይህን ማድረግ አልችልም” ያሉትን ዘንግተዉ በቀጭን ትህዛዝ ፋሺስቶችን ከእስር ቤት በመፍታት ዋሽተዋል። የዋሸ ደግሞ ዉሸታም ነዉ። ስለሁሉም አዝናለሁ። ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! መኮንን ብሩ (ዶ/ር)

ምሕረት ሲሉ : ፍትሕ ስንል ለየቅል!!! – ከቴዎድሮስ ሃይሌ

January 9, 2022
የታማሚው የበሽታ ውጤት መክፉት ያስጨነቀው ዶክተር በደንበኛው ላይ ሊያስከትል የሚችለውን የአካልስቃይና የሞራል ስብራት አለሳልሶ በዘዴ ለመንገር መላ ይዘይዳል:: ታማሚውም ዶክተሩን ሲመለክት እንዴት ነውጤናዬ ሲል

ኢትዮጵያ በታሪኳን እንደ ዐቢይ አሕመድ አይነት እቡይና ፍጹም አምባገነን አጋጥሟት አያውቅም! – አቻምየለህ ታምሩ

January 9, 2022
በኢትዮጵያውያን ሕይዎት እንደሚቀልደው እንደ ከሀዲው ዐቢይ አሕመድ አይነት ፍጹም ስልጣን የነበረው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት፣ ፕሬዝደንትና ጠቅላይ ሚኒስትር አልነበረም። በነገሥታቱ ዘመን እያንዳንዱ መንግሥታዊ ውሳኔ ሲወሰን
1 85 86 87 88 89 250
Go toTop