በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ላይ መፈንቅለ መንግስት ተደረገ የሚል የፌዴራል መንግስቱ ድራማ ሴራ የተቀላቀለባት መሆኗ ነጋሪ አያሻም። የክልሉ መንግስትና በባህር ዳር ያሉ ሚዲያዎች ሳይናገሩት የፌዴራል መንግስት ተዘጋጅቶ ይጠብቅ የነበረውን መግለጫ መስጠቱ የሽፍጥ ፖለቲካው አካል ለመሆኑ ምስክር አያሻውም። የመከላከያ ሰራዊት ዝግጁ ሆኖ በሰዓቱ በቦታው መገኘቱና ለተለያዩ ሃገራዊ ጉዳዮች መግለጫ ለመስተት አሻፈረኝ የሚሉ እነ ንጉሱ ጥላፉን በብርሃን ፍጥነት ስለመፈንቅለ መንግስት መደስኮራቸው የተሴረውን ተንኮል ፍንትው አድርጎ ያሳያል። መመታት መገደል መታሰር ያለባቸውን አፋፍሶ ለማሰር ያልተመቸው የፌዴራል መንግስቱ የወጠናት ሴራ መሆኑን ማንም የፖለቲካ ተንታኝ አያስፈልገውም። ኢሕአዴግ በእንዲህ አይነቱ የፖለቲካው ድራማ ይታወቃል። ይህንን ሴራ ተከትሎ በቁጥጥር ስር የሚውሉትን ኢሕአዴግ ጠላት ብሎ የፈረጃቸውን ሰዎች በመመልከት ብቻ በመፈንቅለ መንግስት ስም የጦዘውን ድራማ ውጤት ማረጋገጥ ይቻላል።
ምንሊክ ሳልሳዊ