ሳዑዲዎች ቀለሉ ኢትዮጵያዉያን እምቢኝ አሉ በዋሽንግተን ዲሲ

November 15, 2013

ኢትዮጵያዉያን ሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት እምቢተኝነታቸዉን አሳይተዋል።መንፈሰ ጠንካራነቱም በጣሙን የላቀ ነበር። አሻፈረኝ ያለ አንድ ኢትዮጵያዊ ፖሊሶቹን አልፎ ወደ ኤምባሲዉ ለመግባት ቢሞክርም ታገተ። ህዝባዊ እንቢተኝነትን ተምሳሊት በማድረግ በርካታ ኢትዮጵያዉያን የኩሩነት እስርን ለመታሰር ሲፈልጉ ታይቷል!…ግን ወሳኝ የሆነ ስምምነት በፖሊሶቹና በኢትዮጵያዉያኑ መካከል ተስተዋለ…ሁለቱም ቡድኖች ቁጣቸዉን የጋራ በሆነ የመፍትሔ ጥላ ስር አኖሩት… በሰላም ስር!
በሳዑዲ አረቢያና በኢትዮጵያ ያሉትን መንታ አንባገነናዉያን ጭካኔ ይገምቱ… የአሜሪካ ፖሊሶች ታጋሽነትን አስተዉለዋልን? የነጻነት ጣእምን አስተዉለዋልን? ይሕንን ነጻነት ነዉ በእናት አገራችን ላይ ለወገኖቻችን የምንሻዉ። በርግጥ ለዉጥ ወደ ሳዑዲ አረቢያና ኢትዮጵያ እያስገመገመ ነዉ! ፍቅርን እንደ ዉድና ብርቅ ቅርስ ይዘዉ በጽናት የሚኖርን ህዝብ ቆስቁሰዋልና የፍቅር ጽኑ መንፈስ እጁን ለ አንባገነናዊ እዉር-ድንብርብርታ አይሰጥም።ህዝቡን አንድ በማድረጋቸዉ እንደሰት…አንድነት ለነጻነትና ፍቅር ጋሻ መከታ ነውና።

Previous Story

“ይህ የኢትዮጵያውያን የውርደት ወር ነው” – ታማኝ በየነ በሳዑዲ ኢምባሲ ደጃፍ ላይ ያደረገው ንግግር (Video)

Next Story

ናይጄሪያ Vs ከኢትዮጵያ፡ ከዋሊያዎቹ ምን እንጠብቃለን?

Go toTop