የኢንተርፖልና ዓለም አቀፍ የፖሊስ ትብብር ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ኢንተርፖል ሰሞኑን አሳልፎ ለኢትዮጵያ መንግስት ስለሰጣቸው 2 ግለሰቦች ያልተሟላ መረጃ ለሚዲያዎች ሰጡ

December 27, 2018

የኢንተርፖልና ዓለም አቀፍ የፖሊስ ትብብር ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ኢንተርፖል ሰሞኑን አሳልፎ ለኢትዮጵያ መንግስት ስለሰጣቸው 2 ግለሰቦች ያልተሟላ መረጃ ለሚዲያዎች ሰጡ::

“ዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል እአአ ከ2014 እስከ አሁን ድረስ 11 ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን አሳልፎ ለህግ ከመስጠት አኳያ ከኢትዮጵያ ጋር በመስራት ላይ ነው፡፡” ያሉት  የኢንተርፖልና ዓለም አቀፍ የፖሊስ ትብብር ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ጸጋዬ ኃይሌ በተለይ ለመንግስታዊው ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በቅርቡ ሁለት ሰዎች ተላልፈው ለኢትዮጵያ የተሰጡ ሲሆን፣ አንደኛው ከባንክ ማጭበርበር ጋር ተያይዞ የሚፈለግ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ ነው፡፡ እኤአ በ2014 እና 2015 ባለው ግዜም ዘጠኝ ተጠርጣሪ ወንጀለኞች  ከተለያዩ አገሮች ለኢትዮጵያ ተላልፈው ተሰጥተዋል፡፡” ብለዋል:: የአንደኛውን ተጠርጣሪ የተከሰሰበትን ወንጀል ቢጠቅሱም ስሙን ያልገለጹት ምክትል ኮማንደሩ ተላልፎ ስለተሰጠው ሁለተኛው ሰው ወንጀልም ማንነትም ሳይገልጹ በደፈናው ሁለት ሰው ተላልፎ ተሰጥቷል በሚል ያልተሟላ መረጃ ለሚዲያ ሰጥተዋል::

በኢንተርፖል ተላልፈው ለኢትዮጵያ መንግስት ሰሞኑን ስለተሰጡ ሁለት ሰዎች ጉዳይ ተጨማሪ ማብራሪያ የሚሰጥ የመንግስት ባለስልጣን አልተገኘም::

https://www.youtube.com/watch?v=rcbWeNfbu_o&t=32s

Previous Story

በዶክተር አብይ የተሾሙት የአምባሳደሮች ምደባ ይፋ ሆነ

Next Story

አባገዳዎች በሚቀጥለው ሳምንት ኦነግን ሊያነጋግሩ ነው

Go toTop