ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባ ሊደረጉ የነበሩት ህዝባዊ ሰልፎች ተራዘሙ

December 14, 2018

(ዘ-ሐበሻ) ነገ ታህሳስ 6 እና ከነገ ወዲያ ታህሳስ 7 በመዲናችን አዲስ አበባ ሊካሄዱ የነበሩት ሕዝባዊ ሰልፎች መራዘማቸው ተገለፀ፡፡ የሰልፎቹ አስተባባሪ ኮሚቴዎች በየፊናቸው ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
የነገ ቅዳሜውን ሰልፍ የጠሩት የቄሮ ፊንፊኔ ኮሚቴ አባላት የነበሩ ሲሆን ሰልፉን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ መስተዳድር ጋር መወያየታቸውን በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡ በውይይታቸውም በሕዝቡ ውስጥ ስለሰልፉ ዓላማ የተለያዩ ሃሳቦች በመኖራቸው፤ በዚህ ሁኔታ ሰልፉን ማካሄዱን ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል በመረዳት እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።
የቄሮ ፊንፊኔ ኮሚቴ አባላት የሰልፉ አላማ በኦሮሚያ የተለያዩ አከባቢዎች በሕዝቡ ላይ እየደረሱ ያሉ የተለያዩ ችግሮች እና መፈናቀሎች እንዲቆሙ መጠየቅ እንደነበር አስታውሰው ሆኖም በማሕበራዊ ሚዲያዎች ብዥታ የሚፈጥሩ መልዕክቶች ሲተላለፉ ማስተዋላቸውን ገልጸዋል። ስለዚህም ሰልፉን ለተወሰነ ጊዜ ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል።
በሌላ በኩል ብሔራዊ አንድነታችን ይጠናከር ሕዝብ ተስፋ ያደረገበትን ለውጥ ለመቀልበስ የሚንቀሳቀሱ አካላት ከድርጊታቸው ይታቀቡ በሚል ሃሳብ ሊካሄድ የታሰበው የእሁዱ ሰልፍ ደግሞ ወደ ታህሳስ 14 ቀን 2011 ዓም መሸጋገሩን አስተባባሪዎቹ ተናግረዋል።
አስተባባሪዎቹ እንዳሉት የሰልፉ ቀን የተቀየረው ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ነው፡:
https://www.youtube.com/watch?v=YJYMYnduprQ

Previous Story

ፍርድ ቤቱ በአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ የቀረበውን የሽብር ክስ ውድቅ አደረገው

Next Story

33 የአዲስ አበባ ወጣቶች በ15 ሺህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ፍርድ ቤት የሰጠው ትእዛዝ ታገደ

Go toTop