በሚኒሶታ ኢሕአዴግ ለቦንድ የተከራየውን አዳራሽ ፖሊስ ከቦታል

August 25, 2013

ፖሊስ የአባይ ቦንድ ይሸጥበታል የተባለውን አዳራሽ ዘግቶ እየጠበቀ(ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታ የቦንድ ሽያጭ ለማከናወን ኢሕ አዴግ የጠራው ስብሰባ ሳይጀመር ብጥብጥ መነሳቱን ዘ-ሐበሻ ከጥቂት ሰዓታት በፊት መዘገቧ ይታወሳል። በስፍራው የሚገኘው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢ እንዳለው ፖሊስ ቦንድ የሚሸጥበትን አዳራሽ ዘግቶ ማንም ሰው እንዳይገባ አድርጓል።
አካባቢው በከፍተኛ የፖሊስ ጥበቃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ፖሊስ ማንም ሰው ስብሰባ እንዳያደርግ ከልክሎ አዳራሹን እየጠበቀ ይገኛል። ኢሕ አዴግ በሚኒሶታ ቦንድ እሸጣለሁ በሚል የላኦ ኮምዩኒቲ አዳራሽን ከ2 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት ፒኤም የተከራየው ቢሆንም ከአባይ በፊት በኢትዮጵያ የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱ፤ የሰብአዊ መብት እንዲከበር፣ መንግስት በ እምነቶች ላይ ጣልቃ እንዳይገባ የሚጠይቁ ወገኖች ባደረሱት ተቃውሞ ፖሊስ አዳራሹን ዘግቶታል።
ኢሕ አዴግን ለመቃወም የመጡ ኢትዮጵያውያን አሁን ድረስ በአካባቢው የሚገኙ ሲሆን በኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ገንዘብ የተመደበላቸውና ወጪ ወጥቶባቸው ወደሚኒሶታ የመጡ ተወካዮች ከአካባቢው ተሰውረዋል።
(ኢትዮጵያውያኑ ከቦንድ መሸጫው አዳራሽ አካባቢ ተሰብስበው እየጠበቁ ነው)
ዘገባውን አሁንም እየተከታተልን እንዘግባለን ይጠብቁን።

Previous Story

Breaking News: በሚኒሶታ ለአባይ ቦንድ ሽያጭ የተጠራው ስብሰባ ሳይጀመር ተበጠበጠ

Next Story

የድምጽ ቃለምልልስ የሚኒሶታውን የአባይ ቦንድ ሽያጭ ካከሸፉት አክቲቪስቶች ጋር (Audio)

Go toTop