ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ሐምሌ 17 ቀን 2008 ፕሮግራም
<... ተስፋሁን ሞተም ሆነ ሌላ ስለኔ የተባለውን አልሰማሁም።ኤርትራ ከገባሁ ጀምሮ ችግር አላገኘኝም እንቅፋትምመቶኝ አያውቅም ስራ ላይ ነበርኩ ስልጠና ላይ የተለያየ ግዳጅ ላይ ነበርኩ።ምንም አልሰማሁም። በአገር ቤትያለውን አሁን በጎንደር ያለውን ግን እሰማለሁ እንከታተላለን። … > ታጋይ ተስፋሁን አለምነህ የቀድሞ የመኢአድየሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ስለሱ በኤርትራ ሞቷል ወይ ታስሯል ስለሚባለው ኤርትራ ደውለን በቀጠሮ ሰሞኑንባነጋገርነው ወቅት ከተናገረው (ሙሉውን ያዳምጡ)
<…ቤተ አማራ በህቡ ይቋቋም እንጂ በአገር ቤትም መሬት ላይ አማራውን ለማደራጀት ይሰራል።አማራው ጠላትብሎ የሚያጠቃውን የሚገለውን ሕወሓትን መታገል ራሱን ከጥቃት መከላከል የሚችለው በአማራነቱ ሲደራጅበአማራ ብሄርተኝነቱ ሲታጠቅ ብቻ ነው ።በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ እንደምታየው አማራው ጋር የጠነከረ የአማራብሄርተኝነት ቢኖር ኖሮ ዛሬ በጎንደር የምታየው ተቃውሞ በቀላሉ ወደሌሎች አካባቢ በፍጥነት ማድረስ ይቻል ነበርዛሬም አማራው ሕወሓት መታገል የሚችለው በአማራነቱ በአንድ ላይ ሲነሳ ነው…ሕወሓት ከ1967 ጀምሮ አማራጠላቴነው ይበል እንጂ የአማራ ሕዝብ የትግራይ ወገኑንም ሆነ ሌላውን አይጠላም ።እኛ ማንም ሕዝብ ጠላት ነውአንልም በአማራ ላይ የተነሳ በአማራ ማንነት ላይ የዘመተው ሕወሓት ግን ጠላታችን ነው…> አቶ መሳፍንትባዘዘው የቤተ አማራ ም/ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ስለ ቤተ አማራና ስለ ወቅታዊው የጎንደር ሕዝባዊእምቢተኝነት ተጠይቆ ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ክፍል አንድን ያዳምጡት)
ሰሞኑን በጥቁር አሚሪካኖች እና በነጭ ፖሊሶች መካከል የተከሰተው ተቃርኖ ከኢትዮጵያዊ(ጥቁር) ቤተሰብትወልዶ በነጭ አሳዳጊዎቹ እቅፍ እያደገ ለሚገኘው ኢትዮጵያዊው ጨቅላ ያለው አንድምታ ሲቃኝ፣”ወደፊትፖሊስ ሆኜ ማህበረሰቡን ማገለገል ጽኑ ምኞቴ ነው “ኢትዮጵያዊው የ6 እመት ህጻን (ልዩ ዘገባ)
ሌሎችም አሉን
ዜናዎቻችን
ታጋይ ተስፋሁን አለምነህ ኤርትራ በወታደራዊ ስልጠና መቆየቱንና ችግር እንዳላገኘው ገለጸ
የአማራ ሕዝብ በአማራነቱ ራሱን አደራጅቶ ካልታጠቀ ከሕወሓት ጥቃት አያመልጥም ተባለ
የትግርይ ክልል በ34ቱ የወልቃይት አማሮች ላይ የብሄር ማንነታቸውን በመናገራቸው ጭምር ከሰሰ
የብአዴን መሪዎች ጎራ ለይተው ቆመዋል የእነ አለምንህ መኮንን ቡድን ለሕወሓት ታማኝነቱን ለማረጋገጥ ሩጫ ላይመሆኑ ተገለጸ
ኢትዮጵያ ከ11 የግብጽ የመደሃኒት አምራቶች ጋር የነበራት ግንኙነትን አቋረጠች
የወልቃይት ነዋሪዎች የማነነት ጥያቄ እንዴት ኣልባት ማግኘት እንደሚችል አንድ የህግ እና የህገ መንግስት ምሁርምክራቸውን ለገሱ
የሰብአዊ መብት ትሟጋቾች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የፖለቲካ ፍጥጫ ወደ ማያባራ ደረጃ እንዳይሸጋገርሰጋታቸውን ገለጹ፣
የአለማችን ቱጃሩ ቢልጊት ኢህአዲግ በዘጎቹ ላይ የሚያድረሰውን የመረጃ የማግኘት መብት አፈናን ከማወገዝተቆጠቡ
የአሜሪካኖች የፕ/ዊ ተፎካካሪዎች ሰሞነኛ ሹመት እና ፍትጊያ አይሏል፡ ሂለሪ ክሊንተን ስፓነሽ ተናጋሪውሲናተርን ምክትላቸው አደርገው ሾሙ” ሁላችሁም እንኳን ወደ አገራቸን በደህና መጣችሁ፣ አሜሪካ የሁላችንአገር ናት “እጩ ም/ል የዲሞክርት ፕሬዘዳንት ቲም ኬይን
ከዶሮዎች ሰውነት የሚወጣው ጠረን ለወባ በሽታ ፍቱን መደሃኒት መሆኑን ሳይንሲስቶች ኢትዮጵያ ውስጥአረጋገጡ