ሀገር የጋራ ነው ሃይማኖት የግል ነው – (የኢትዮ-ካናዳዊያን የዲሞክራሲ መድረክ በኦታዋ ካናዳ)

February 19, 2013

የኢትዮ-ካናዳዊያን የዲሞክራሲ መድረክ በኦታዋ ካናዳ ባወጣው የአቋም መግለጫ ሃገር የጋራ ነው ሃይማኖት የግል ነው። ይህንን ጥንታዊ የአባቶች ብሂል የሚያናውፀው ምንም ሃይል የለም አይኖርምም። ማሸበር፣ ማፈራረስ የዘወትር ተግባሩ የሆነው የወያኔ አምባገነን መንግስት በባህል፣ በታሪክ፣ በቋንቋና በደም የተሳሰሩ ሕዝቦችን በሃይማኖትና በጎጥ በመከፋፈል ኢትዮጵያውያን ለሠላም፣ ለፍቅር፣ ለአንድነትና ለወንድማማችነት ያላቸውን የቃል ኪዳን ትስስር ለመበጣጠስ ሌት ተቀን ይማስናል።የወያኔ አምባገነን መንግስት ሁለቱን ታላላቅ ሃይማኖቶች ክርስትናውና እስልምናው ተከባብረውና ተሳስበው በመኖር ለዘመናት ያስቆጠሩትን ትስስር ለመናድና ብጥብጥ ተነስቶ ደም እንዲቃቡ፣ በዚህም አጋጣሚ የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም እንቅልፍ አጥቶ የተንኮል ሴራውን እየቀፈቀፈ ነው።” አለ። ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

 

Previous Story

የአቶ በረከት ኮሚኒኬተሮች የአቶ ጁነዲንን የመቀላቀል ጥያቄ ውድቅ አደረጉ

Next Story

የካቲት 12 የሰማዕታት ቀን ተከበረ፤ አርበኞች የግራዚያኒ ሐውልት እንዲፈርስ ጠየቁ

Go toTop