የካቲት 12 ቀን 2005 ዓ. ም. የሰማዕታት ቀን በአዲስ አበባ ሲከበር የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ተወካይ ባደረጉት ንግግር የግራዚያኒ ሐውልት እንዲፈርስ ጠየቁ። የአርበኞቹ ተወካይ ባደረጉት ንግግር ላይ ”
“የፋሽስቱ መሪ ቤኒቶ ሙሶልኒ በኢትዮጵያና በጣሊያን ሕዝቦች ላይ ያደረሰው ግፍ ወደር የላሌው እንደነበር በሕይወት ያለና የታሪክ ተመራማሪዎች በታሪክ መዛግብት የሰጡት የምስክርነት ቃል አረጋግጡዋል፡፡ በጣሊያን አገር በመጨረሻዋ ሰዓት ሙሶሉኒ በጣሊያን አርበኞች እጅ እንዲይወድቅ ሲቅበዘበዝ ተይዞ በጥይት ከተደበደበ በሁዋላ ሬሳው ወደ ሚሊን ተወስዶ ተዘቅዝቆ መሰቀሉ ምን ያህሌ ህዝብ እንደጠላው ያሳያል፡፡ ይህን ግፈኛ ዛሬ ሙሶሉኒ በሰው ላይ ጥይት ተኩሶ አያውቅም ፤መልካም አስተዳዳሪ እንደነበር የሚመሰክሩ የጣሊያን ፖለቲከኞች ቀና ቀና ማለት ጀምረዋል፡፡” ብለዋል።
ሙሉውን ንግግር ለማንበብ እዚህ ይጫኑ