9 የትግራይ ተወላጆች በአሶሳ ተገደሉ

May 15, 2014

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ በፌስቡክ ገጹ እንደዘገበው፦ ባለፈው ሳምንት የጉልበት ሥራ ለመስራት በአንድ ኮንትራክተር ተቀጥረው ወደ አባይ ግድብ በደህንነት መኪና ሲጓዙ ከነበሩ 28 የትግራይ ተወላጆች ዉስጥ ዘጠኙ ታርደው ሲገደሉ የተወሰኑም ቆስለዋል።

ባለፈው ቅዳሜ ደግሞ አንድ የትግራይ ተወላጅ በተመሳሳይ ተገድሎ ተገኝቷል። ቀጥሎም በአንድ ድርጅት ሲሰሩ የነበሩ ሦስት ሰራተኞች መገደላቸው ተሰምቷል። ገዳዮቹ ከኢህአዴግ ጋር የተጣላ የአንድ ዓማፂ ቡድን አባላት ናቸው። ባከባቢው የፌደራል ፖሊሶችና መከላከያ ሰራዊት አባላት ቢገኙም ወንጀሉ መከላከል እንዳልቻሉ ታውቋል። ሁኔታው ለማረጋጋት ሲሉ አቶ ፀጋይ በርሀና አቶ አዲሱ ለገሰ ወዳከባቢው ቢጓዙም የተለመደ ፖለቲካ ከመስበክ የዘለለ ነገር አላደረጉም።

መንግስት ፀጥታን ማስከበር ይገባዋል። ደግሞ ሰለማዊ የቀን ሰራተኞች በደህንነት መኪና መጫን ተገቢ አይደለም። በደረሰ ጉዳት ጥልቅ ሐዘን ይሰማናል።

ወላዲት ትግራይ መዓዝ ይኾን ሓዘንኪ ዘብቅዕ?

Previous Story

በስደት ያለው ሲኖዶስ ሐዲስ ሐዋርያ አባ ወልደትንሣኤን የክፍለዘመኑ የሰላም አባት ሲል ሸለመ

Next Story

‹‹ዛቻና ማስፈራራት ይገጥሙናል›› አቶ ዓሊ ሱሌማን፣ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር

Go toTop