(ፎቶ ከፋይል)
ድምጻችን ይሰማ እንደዘገበው፦
በዛሬው እለት ችሎት የቀረቡት በግፍ እስር ላይ የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ከብዙ ማመላለስና ማጉላላት በኋላ የጥፋተኝነት ብይን የተሰጠባቸው መሆኑ የታወቀ ሲሆን ለግንቦት 15/2006 መከላከያቸውን እንዲያቀርቡ ተቀጥረዋል።
የተማረውን ሐይል ለበጎ አላማ የመጠቀም ሀላፊነት ያለበት መንግስት በሃሰት ክስና በከፍተኛ ስቃይ ተማሪዎችን ሲያጉላላ መቆየቱ ሳያንሰው የጥፋተኝነት ብይን ማስተላለፉ በታሪክ የሚያስወቅሰው አሳፋሪ ወንጀል ነው:: የካንጋሮው ፍርድ ቤት ውሳኔ ዛሬም ፍትህን አቁስሏታል።