(ዘ-ሐበሻ) በሸዋ ኢንተርቴይመንት እና በድምፃዊ ጎሳዬ ቀለሙ (ጃኪ ጎሲ) ዙሪያ ባለው አለመግባባት ዛሬ ፍድር ቤት ቀርበው፤ ሸዋ ኢንተርቴይመንት ያቀረበው የኮንሰርቱ ይቁም ጥያቄ በፍርድ ቤቱ ውድቅ እንዳደረገው ዘ-ሐበሻ ጠዋት ላይ ዘግባ እንደነበር ይታወሳል። ጃኪ ጎሲ ከፍርድ ቤቱ የኮንሰርቱ ይደረግ ውሳኔ በኋላ በፌስቡክ ገጹ “እውነት ወጣች” ሲል ሲገልጽ ሸዋ ኢንተርቴይመንት ባለቤት አቶ ሸዋ ኢተና በበኩሉ “ጃኪ ድል አላደረገም፤ ኮንሰርቱ ቢደረግ በሕይወታችሁ ላይ የሚያደርስባችሁ ጉዳት ምንድን ነው? በሚል ዳኞቹ ኮንሰርቱ እንዲደረግ ቢፈቅዱም፤ ገና የፍርድ ቤቱ ሂደት መታየት ጀመረ እንጂ አላለቀም” ሲል ለዘ-ሐበሻ ገልጿል። በቀጣይ ቀጥሮዎች ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ማየት እንደሚጀምር የገለጸው ሸዋ የ500 ሺህ ዶላር ካሳ ጥያቄ እንዳቀረበም ለዘ-ሐበሻ አረጋግጧል።
አጭሩን ቃለምልልስ ያድምጡ፤ ጃኪ የሚሰጠውን ምላሽ ዘ-ሐበሻ ትጠብቃለች።