[ሰበር ዜና] በአዲስ አበባ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ

April 22, 2014

ሰማያዊ ፓርቲ ለ19/2006 ዓ.ም ለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፉ ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ በአስሩም ክፍለ ከተሞች ቅስቀሳ የጀመረ ሲሆን በአብዛኛዎቹ ክፍለ ከተሞች ቅስቀሳው እየተካሄደ እንደሚገኝ ከሰልፉ አስተባባሪዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡

ይሁንና በአንዳንድ አካባቢዎች ፖሊስና ደህንነቶች ቅስቀሳውን ለማስቆም የሞከሩ ሲሆን በካሳንችስ፣ አቧሬና አራት ኪሎ መስመር ሲቀሰቅሱ የነበሩ አባላትና ደጋፊዎች በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ካሳችንችስ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኙም ለማውቅ ተችሏል፡፡

ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን እንመለሳለን።

Previous Story

Sport: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በወር 15ሺህ ዶላር ደመወዝ ፖርቱጋላዊ አሰልጣኝ ቀጠረ

Next Story

ነገረ -ኢትዮጵያ ጋዜጣ ከወቅታዊ ዜናዎችና ትንታኔዎች ጋር – ቁጥር 9 [PDF]

Go toTop