ትልቁ ጥፋታችን ስልጣኑን ለአብይ አህመድ መስጠታችን ነው።” ዶ/ር ገዱ አንዳርጋቸው March 5, 2025 ዜና Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email ትልቁ ጥፋታችን ስልጣኑን ለአብይ አህመድ መስጠታችን ነው።” ዶ/ር ገዱ አንዳርጋቸው ይሕን ሀውልት የሆነ ንግግር የቻለ ህሉ ያድምጠው!አማራን በደንብ ነው የገለጸው!pic.twitter.com/WgfnUXH2ib — “I swear I will never be Amhara Again “ (@MulugetaGetah10) March 6, 2025 Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email 3 Comments እንዴት አይነት ሃፍረተ ቢስ ነው ለወያኔ ሲጎነበስ ከርሞ ለአብይ ሲጎነበስ ከርሞ ጢባ ጢቤ ሲጫወቱበት የነበሩትን ትግሬዎች ምንም አላጠፋችሁም ብሎ ተምበርክኮ ለምኖ ይቅርታ ጠይቆ አሁን ምን ቀርቶት ነው ወደ ሚዲያ የወጣው እናንተ ካላፈራችሁ እፍረትን ከየት እንማር? Reply እጅግ ያሳዝናል። 27 ዓመት የወያኔ አገልጋይ የነበረ ሰው አሁን ውጭ ላይ ሆኖ ጥፋታችን ስልጣኑን ለአብይ አህመድ መስጠታችን ነው ይላል። በወያኔ ጊዜ የአማራ ህዝብ ሁለተኛ ዜጋ አልነበረም? ያንን አረመኔ ስርዓት አላገለገልክም እንዴ? ያኔ ማን ያዘህ ሃገር ጥሎ ለመፈርጠጥ። የወያኔ መንጋ እንደፈለገ ሲነዳው የነበረ ባለስልጣን አሁን ለአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ ሆኖ መቅረቡ ንስሃ ነው ኑዛዜ? በ 27 ዓመቱ የወያኔ የመከራ ዘመን ያለቀው የአማራ ህዝብ ቁጥር ስንት ነው? ለዚህ ነው ፓለቲካችን ሁሉ የቁም ቅዥት የሚሆነው። ካለፈው መልካም ነገርም ሆነ ክፉ ነገር ሳንማር በፊታችን ያለውን ለመገፍተር ስለምንፍጨረጨር። እርግጥ ነው ብልጽግና ከወያኔ የክፋት ኮሮጆ ያፈተለከ በመሆኑ ያኔ ሰው ጠ/ሚሩን ሲያመልክና በዘፈንና በቀረርቶ ሲያሞካሽ ተው ረጋ በሉ የሃበሻ ፓለቲካ ችግሩ ጅምሩ አይደለም። መሃሉና ፍጻሜው ግን ኦሮማይ ነው ስንላቸው ሃሳባችን የገፈተሩ የስሜት ፓለቲከኞች ዛሬ ላይ ተመልሰው ብለኸን ነበር ሳናስተውል ቀርተን ነው ይላሉ። እንግዲህ ያለፈም ሆነ የአሁን አሞጋሽና የብልጽግና ደጋፊ ነገሮችን ማየት ያለበት እንዴት ያስተዳድራል እንጂ ከየትኛው ብሄር መጣ መሆን የለበትም። የሃገራችን ሰዎች ከወያኔ ጋር የነበራቸው ፍትጊያ ከትግራይ ስለመጡ አይደለም። አስተዳደራቸው አረመኔና ከፋፋይ ስለነበረ እንጂ። የአድዋ ጦርነት ከማን ጋር ነው ኢትዮጵያ የተዋጋችው ተብለው የተጠየቁ ወጣቶች ከኬኒያ ጋር ብለው ሲመልሱ መስማት ለጀሮ ይቀፋል። ግን በሻቢያና በወያኔ የፓለቲካ ፋፋ ያደጉ ልጆች ታሪክ አንበው ለመረዳትም ሆነ ያለፈን ከቆመ ጠይቆ ለመማር ጊዜ የላቸውም። ቲክቶክ ላይ ተጥዶ የሚውል ሙት ትውልድ! ለነገሩ በብሄሩ የተሳከረ ትውልድ ግራና ቀኝ ማወቁም የሚያስገርም ነው። ታዲያ እንዲህ ያለውን ትውልድ ይዘው ነው የፋኖ፤ ኦነግ ገለ መሌ የብሄር ትግል የሚሉን። ማወቅ ጉልበት መሆኑ ቀርቶ ድንቁርናና ጠበንጃ ይዞ እንዘጥ እንዘጥ ማለት የመኖሪያ ብልሃት ማስገኛ ሆኗል። 40 ዓመት ሙሉ ቱርክን ሲፋለም የነበረው (Kurdistan – PKK) በሰላማዊ መንገድ ልዪነቱን ለመፍታት የሰላም ጥሪ ካደረገ እንዴት ነው እኛ እድሜ ልክ እየገደልና እያስገደልን የምንኖረው? መገዳደል ይብቃ። ወያኔዎችም እረፉ፤ ፋኖዎችም ተው/ኦነግም ይብቃችሁ። ህዝባችን ባይሆን እንኳን ሰላም አግኝቶ በባዶ ሆድም ቢሆን በሰላም ይተኛበት። በድሮንና በዲሽቃ፤ በታንክ አታስቀጥቅጡት። በህዝብ መሃል እየተወሸቃችሁ የሣርና የጭቃ ቤት በድሮን አታስመቱ! ስንት የተለፋበትን የሰሊጥ ምርት ማቃጠልም ለአማራ ህዝብ ነጻነት መዋጋት አይደለም። አረመኔነት እንጂ! ግን ሰው ለማስመረር፤ አብሮ እንዲሰለፍ ለማስገደድ የሚጠቀሙበት የሙት የፓለቲካ ብልሃት በመሆኑ እነርሱንም ሆነ ነጻ እናወጣዋለን የሚባለውንም ህዝብ ይዞ ይጠፋል። በመዝጊያው አቶ ገድ ያለፈበትን የወያኔና የብልጽግና ዘመን ተግባሩንና ትውስታውን ሁሉ በዝርዝር በመጽሃፍ መልክ ምንም ሳይደብቅ ሊያጋራን ይገባል። እኛ እናልፋለን። ግን ቀሪ ትውልድ ልብ ገዝቶ ማወቅን ሲሻ የሚያገላብጠው የታሪክ ድርሳን ጥሎ ማለፍ መልካም ይመስለኛል። በሌላ በኩል አቶ ገድ ትላንት ወያኔና ብልጽግናን አገልግሏልና አሁን ለሃገሩና ለወገኑ ምንም ማድረግ አይችልም እያልኩም አይደለም። ይቻላል/ይችላልም። ግን ካለፈው እንማር። የምንደበቀው ነገር አይኑር። ምን አልባት በህይወት እያለን መውጣት የሌለበት ሚስጢርም ከሆነ አፈር ከተመለሰብን በህዋላ ታትሞ እንዲወጣ ሁሉን ነገር እውነትን ብቻ ተመርኩዘን እንጻፍ። ለቀሪ ትውልድ እናሳውቅ። በተረፈ በእኔ እምነት ብልጽግናም ተገዶም ሆነ በውድ ቢወርድ የተሻለ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ ይመጣል ብዬ አላምንም። ያ እንዳይሆን የክልል ፓለቲካው፤ ከብሄርና ከቋንቋ አምልኮቱ ጋር ተዳብሎ ጭራሽ አያራምድም። ዳግመኛ ሃገራችን የወረረው ጣሊያን የተጠቀመበትን አሰራር እንዳለ ቀድተው ነው ወያኔዎች ሥራ ላይ ያዋሉት። እኛ ስንቧቀስ እነርሱ ሊኖሩ/ብልጽግናም ያንኑ አሰራር ነው የሚከተለው። እንዲያውም ከወያኔ አሰራር በይዘትም/በጥልቀትም ባይከፋ፡ አበስ ገበርኩ። አይ ሃገር…ሁሌ መራኮት! በቃኝ Reply አረጋዊ በርሄ፣አብረሀም በላይ፣አባዱላ ገመዳ፣በቀለ ገበሮ (ለጊዜው ህክምና ላይ ነው)፣ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያን ላጠፉበት ምቾታቸው ተከብሮ የቆዩ ወንጀለኞችናቸው።ፕሮዚደንቷ የተሾሙ ሰሞን ዶር ሙላቱን ለመከላከል ላይ ታች ሲሉ ነበር አብይ መጥጦ በውርደት ወረወራቸው እንጅ አብይ በመጻፍ ገልጾታል ጭድ ስጠው ገደሉን አያይም ብሎ። ከነዚህ ሆዳሞች መሀል በቀዳሚነት ዶር ይልቃል፣ንጉሱ ጥላሁን፣ደመቀ መኮንን፣ገዱ አንዳርጋቸውን የመሳሰሉ ይገኙበታል። መቼም አገኘሁ ተሻገርን ረስተነው አይደለም በራሱም የተረሳ በመሆኑ እንጅ። ለማንኛውም አረጋዊ በርሄ አ አ የሚያስቀምጠው አንዳችም ምክንያት ባለመኖሩ ከሆነለት መቀሌ ሂዶ ፓርቲ ያቋቁም ከሆነለት አዲስ አበባ ቁጭ ብሎ ባያላግጥ መልካም ነው። Reply Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Previous Story የአድዋ ድል መታሰቢያ በሽመልስ አማረ Next Story ጠቃሚ ጽንስ በቀላሉ አይወለድም! – ይነጋል በላቸው
እንዴት አይነት ሃፍረተ ቢስ ነው ለወያኔ ሲጎነበስ ከርሞ ለአብይ ሲጎነበስ ከርሞ ጢባ ጢቤ ሲጫወቱበት የነበሩትን ትግሬዎች ምንም አላጠፋችሁም ብሎ ተምበርክኮ ለምኖ ይቅርታ ጠይቆ አሁን ምን ቀርቶት ነው ወደ ሚዲያ የወጣው እናንተ ካላፈራችሁ እፍረትን ከየት እንማር? Reply
እጅግ ያሳዝናል። 27 ዓመት የወያኔ አገልጋይ የነበረ ሰው አሁን ውጭ ላይ ሆኖ ጥፋታችን ስልጣኑን ለአብይ አህመድ መስጠታችን ነው ይላል። በወያኔ ጊዜ የአማራ ህዝብ ሁለተኛ ዜጋ አልነበረም? ያንን አረመኔ ስርዓት አላገለገልክም እንዴ? ያኔ ማን ያዘህ ሃገር ጥሎ ለመፈርጠጥ። የወያኔ መንጋ እንደፈለገ ሲነዳው የነበረ ባለስልጣን አሁን ለአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ ሆኖ መቅረቡ ንስሃ ነው ኑዛዜ? በ 27 ዓመቱ የወያኔ የመከራ ዘመን ያለቀው የአማራ ህዝብ ቁጥር ስንት ነው? ለዚህ ነው ፓለቲካችን ሁሉ የቁም ቅዥት የሚሆነው። ካለፈው መልካም ነገርም ሆነ ክፉ ነገር ሳንማር በፊታችን ያለውን ለመገፍተር ስለምንፍጨረጨር። እርግጥ ነው ብልጽግና ከወያኔ የክፋት ኮሮጆ ያፈተለከ በመሆኑ ያኔ ሰው ጠ/ሚሩን ሲያመልክና በዘፈንና በቀረርቶ ሲያሞካሽ ተው ረጋ በሉ የሃበሻ ፓለቲካ ችግሩ ጅምሩ አይደለም። መሃሉና ፍጻሜው ግን ኦሮማይ ነው ስንላቸው ሃሳባችን የገፈተሩ የስሜት ፓለቲከኞች ዛሬ ላይ ተመልሰው ብለኸን ነበር ሳናስተውል ቀርተን ነው ይላሉ። እንግዲህ ያለፈም ሆነ የአሁን አሞጋሽና የብልጽግና ደጋፊ ነገሮችን ማየት ያለበት እንዴት ያስተዳድራል እንጂ ከየትኛው ብሄር መጣ መሆን የለበትም። የሃገራችን ሰዎች ከወያኔ ጋር የነበራቸው ፍትጊያ ከትግራይ ስለመጡ አይደለም። አስተዳደራቸው አረመኔና ከፋፋይ ስለነበረ እንጂ። የአድዋ ጦርነት ከማን ጋር ነው ኢትዮጵያ የተዋጋችው ተብለው የተጠየቁ ወጣቶች ከኬኒያ ጋር ብለው ሲመልሱ መስማት ለጀሮ ይቀፋል። ግን በሻቢያና በወያኔ የፓለቲካ ፋፋ ያደጉ ልጆች ታሪክ አንበው ለመረዳትም ሆነ ያለፈን ከቆመ ጠይቆ ለመማር ጊዜ የላቸውም። ቲክቶክ ላይ ተጥዶ የሚውል ሙት ትውልድ! ለነገሩ በብሄሩ የተሳከረ ትውልድ ግራና ቀኝ ማወቁም የሚያስገርም ነው። ታዲያ እንዲህ ያለውን ትውልድ ይዘው ነው የፋኖ፤ ኦነግ ገለ መሌ የብሄር ትግል የሚሉን። ማወቅ ጉልበት መሆኑ ቀርቶ ድንቁርናና ጠበንጃ ይዞ እንዘጥ እንዘጥ ማለት የመኖሪያ ብልሃት ማስገኛ ሆኗል። 40 ዓመት ሙሉ ቱርክን ሲፋለም የነበረው (Kurdistan – PKK) በሰላማዊ መንገድ ልዪነቱን ለመፍታት የሰላም ጥሪ ካደረገ እንዴት ነው እኛ እድሜ ልክ እየገደልና እያስገደልን የምንኖረው? መገዳደል ይብቃ። ወያኔዎችም እረፉ፤ ፋኖዎችም ተው/ኦነግም ይብቃችሁ። ህዝባችን ባይሆን እንኳን ሰላም አግኝቶ በባዶ ሆድም ቢሆን በሰላም ይተኛበት። በድሮንና በዲሽቃ፤ በታንክ አታስቀጥቅጡት። በህዝብ መሃል እየተወሸቃችሁ የሣርና የጭቃ ቤት በድሮን አታስመቱ! ስንት የተለፋበትን የሰሊጥ ምርት ማቃጠልም ለአማራ ህዝብ ነጻነት መዋጋት አይደለም። አረመኔነት እንጂ! ግን ሰው ለማስመረር፤ አብሮ እንዲሰለፍ ለማስገደድ የሚጠቀሙበት የሙት የፓለቲካ ብልሃት በመሆኑ እነርሱንም ሆነ ነጻ እናወጣዋለን የሚባለውንም ህዝብ ይዞ ይጠፋል። በመዝጊያው አቶ ገድ ያለፈበትን የወያኔና የብልጽግና ዘመን ተግባሩንና ትውስታውን ሁሉ በዝርዝር በመጽሃፍ መልክ ምንም ሳይደብቅ ሊያጋራን ይገባል። እኛ እናልፋለን። ግን ቀሪ ትውልድ ልብ ገዝቶ ማወቅን ሲሻ የሚያገላብጠው የታሪክ ድርሳን ጥሎ ማለፍ መልካም ይመስለኛል። በሌላ በኩል አቶ ገድ ትላንት ወያኔና ብልጽግናን አገልግሏልና አሁን ለሃገሩና ለወገኑ ምንም ማድረግ አይችልም እያልኩም አይደለም። ይቻላል/ይችላልም። ግን ካለፈው እንማር። የምንደበቀው ነገር አይኑር። ምን አልባት በህይወት እያለን መውጣት የሌለበት ሚስጢርም ከሆነ አፈር ከተመለሰብን በህዋላ ታትሞ እንዲወጣ ሁሉን ነገር እውነትን ብቻ ተመርኩዘን እንጻፍ። ለቀሪ ትውልድ እናሳውቅ። በተረፈ በእኔ እምነት ብልጽግናም ተገዶም ሆነ በውድ ቢወርድ የተሻለ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ ይመጣል ብዬ አላምንም። ያ እንዳይሆን የክልል ፓለቲካው፤ ከብሄርና ከቋንቋ አምልኮቱ ጋር ተዳብሎ ጭራሽ አያራምድም። ዳግመኛ ሃገራችን የወረረው ጣሊያን የተጠቀመበትን አሰራር እንዳለ ቀድተው ነው ወያኔዎች ሥራ ላይ ያዋሉት። እኛ ስንቧቀስ እነርሱ ሊኖሩ/ብልጽግናም ያንኑ አሰራር ነው የሚከተለው። እንዲያውም ከወያኔ አሰራር በይዘትም/በጥልቀትም ባይከፋ፡ አበስ ገበርኩ። አይ ሃገር…ሁሌ መራኮት! በቃኝ Reply
አረጋዊ በርሄ፣አብረሀም በላይ፣አባዱላ ገመዳ፣በቀለ ገበሮ (ለጊዜው ህክምና ላይ ነው)፣ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያን ላጠፉበት ምቾታቸው ተከብሮ የቆዩ ወንጀለኞችናቸው።ፕሮዚደንቷ የተሾሙ ሰሞን ዶር ሙላቱን ለመከላከል ላይ ታች ሲሉ ነበር አብይ መጥጦ በውርደት ወረወራቸው እንጅ አብይ በመጻፍ ገልጾታል ጭድ ስጠው ገደሉን አያይም ብሎ። ከነዚህ ሆዳሞች መሀል በቀዳሚነት ዶር ይልቃል፣ንጉሱ ጥላሁን፣ደመቀ መኮንን፣ገዱ አንዳርጋቸውን የመሳሰሉ ይገኙበታል። መቼም አገኘሁ ተሻገርን ረስተነው አይደለም በራሱም የተረሳ በመሆኑ እንጅ። ለማንኛውም አረጋዊ በርሄ አ አ የሚያስቀምጠው አንዳችም ምክንያት ባለመኖሩ ከሆነለት መቀሌ ሂዶ ፓርቲ ያቋቁም ከሆነለት አዲስ አበባ ቁጭ ብሎ ባያላግጥ መልካም ነው። Reply