ዝንጀሮን ያህል አያፍሩ!

May 13, 2024

ትናንት አሳሂ መሲህ ከሀዲዎችን ጭራቅን ያመለኩቱ፣

ዛሬ የእውነት ሀዋርያ መስለው ሕዝብ ሌት ተቀን ሲሰብኩ፣

የቅጠል በጣሽ ፍየልን ያህል እንኳ ትንሽ ለአንድ አፍታ አያፍሩ፡፡

 

በብር ዲናር እየተገዙ ሕዝብን ለሰላሳ ዓመት ያሳረዱቱ፣

ዛሬ ተራ በተራ በአለቆቻቸው እንደ ጉልቻ ተገፍተው ሲፈነገሉ፣

የይሁዳን ያህል ፀፀት በልቷቸው ራሳቸውን አንቀው አይገሉ!

 

ፍሪንባ ዝልዝል እቆረጡ ቢራና ድራፍት እየጨለጡ፣

ባዶ ሆድ በወኔ ሞልተው ጭራቆችን የገጠሙትን ሲተቹ፣

ማሰብ የማይችሉትን የጋማ ከብቶችን ያህል አያፍሩ፡፡

 

ብዙ ሺህ ማይል እርቀው የበርገር ክምር የሚግጡቱ፣

ቆሎ ቆርጥሞ ፋሽሽት ያሸናን አርበኛ ያለመታከት ሲነቅፉ፣

በቃኝን የማያውቀውን የአሳማን ያህል ይሉኝታ እሚባል አያውቁ!

 

ሆድ እንደ ቅሪላ ሞላልተው ትምክ ተሚል አልጋ ውስጥ እያሉ፣

ድንጋይን ትራስ አድርጎ ባንዳና ጭራቅ የሚፋለምን ፋኖ ሲተቹ፣

አዙሮ ማያ አንገት የነፈገውን የእርጉሙን የእባብን ያህል አያፍሩ፡፡

 

ፋኖ ባህር ዳር ገባ ሲባሉ እንደ ኮርማ ቀንድ ሻኛ የሚያወጡቱ፣

ለስልት ለቆ ወጣ ሲባሉ እንደ ቡችላ ጅራት ወትፈው የሚጠፉቱ፣

በፋኖ የትችት የወቀሳ መርዝ ሲተፉ ከቶ ምን ይሉኝ አያውቁ፡፡

 

ቅልጥ ታለው ከተማ ውስኪና ኮኛክ ሌት ተቀን እየጨለጡ፣

ፋኖ እዚህ ግባ ተዚያኛው ስፍራ ና ውጣ እያሉ ሲወሸክቱ፣

የጦጣን ያህል ይሉኝታ የላቸው ዝንጀሮን ያህል አያፉሩ!

 

 

 

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

ግንቦት ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ.ም.

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

አብይ ከፋኖ ጥይት ለጥቂት አመለጠ | ሰራዊቱ ጎጃም ላይ ተከበበ | ባለሀብቱ ጅቡቲ ላይ ተያዘ

Next Story

አብይ ከሞርታር ጥቃት | “ከማለቃችን በፊት ድረሱ” ጄ/ል ዘውዱ | አዲስአበባ ፋኖ ከባድ መግለጫ | እነ ጌታቸው ረዳ ሽጉጥ ተማዘዙ | “ፋኖን አሸንፈናል እንቅስቃሴው ተገቷል” አብይ – “የውርደት ካባ አስለብሰናቸዋል” የፋኖ ምላሽ | የባህርዳር ከተማ ባለስልጣናት በፋኖ እጅ ወደቁ

Go toTop