መታደግ ለኢሀዴግ  ወይስ ለአገር ?

November 16, 2023

ኢትዮጵያ ከድህረ ኢህአዴግ ጀምሮ ሠላም እና መረጋጋት የሚባል ነገር እንደራቃት መኖሯን የሚካድ ባይሆንም  እንደዛሬዉ በይፋ አበጀን ጦርነት  መባሉ ግን ጦርነት ለምን እና ለማን ብሎ መወሰን የፖለቲካ ጥቅም ማስጠበቂያ መሳሪያ ሲሆን በግልፅ ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያ ያልተፈለገ እና ያልተጠበቀ ጦርነት በተለያዩ ጊዜያት ሲደረግ በአገሪቷ እና ህዝቧ ላይ ከፍተኛ መከራ እና ስቃይ ቀንበር ጭኖ ከማለፉ በስተቀር የታደገዉ ነገር አለመኖሩን ከታሪክ እና ካለፉት የመከራ ዘመናት መማር ይቻላል፡፡

በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ከሰባ አስከ መቶ ሽ የሠዉ  ህወት እና የአካል ጉዳት ደርሷል፤ ባድመን መረቀናል ፣በ1997  ዓ.ም. በተደረገ ምርጫ የምርጫዉን ነፃ እና ገለልተኛነት መና መሆኑን በአደባባይ የተረጋገጠ ዕዉነታ መሆኑ ፣ በትግራይ /ትህነግ ወረራ  በተካሄደ ጦረትነት የተከፈለዉ መስዋዕትነት እና ቁስል ሳይሽር  በአማራ  ህዝብ ላይ „“በጥቁር ጠበንጃ “  በተፈጠረ አንጃ  በህዝብ ላይ የተላለፈ የጦርነት  ፍርጃ የአካባቢዉን ህዝብ እና የአገር ሀብት ከማዉድም ዉጭ ጦርነቱ የታደገዉ ነገር አለመኖሩን ከጦርነቱ ዉጤት በላይ ምስክር ሊኖር አይችልም ፡፡  መታደጉ ለኢህአዴግ / ብአዴን ከሆነ ሀቅ ነዉ ፡፡

በአጭሩ በኢትዮጵያ ከድህረ ኢህአዴግ አስካ ዛሬ የተካሄዱ ጦርነቶች ሁሉ የኢህዴግን ስልጣን ጊዜ ለማራዘም የተደረገ በመሆኑ ከላይ በህግ ማስከበር ስም እና ምርጫ  ’97 ማግስት በህዝብ ላይ ለደረሱት እና እየደረሱ ላሉት መጠነ ሰፊ  ዉስብስብ ችግሮች የኃይል አማራጭ ለአገር እና ህዝብ ከለላ እና ጥበቃ መፍትሄ ሲሆን ታይቶ ፤ተስምቶ  አይታወቅም ፡፡

ኢትዮጵያ እና ህዝቧ “የዕስር እና አሳር ምድር ” በሆነችበት በተለይም በኢትዮጵያዊነት ማንነት ጠላትነት በሆነበት  የዓማራ ህዝብ ላይ ከለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት አስቀድሞ አስካሁን በሚደርስ ሁለንተናዊ በደል የአገሪቷን አንድ ሶስተኛ የእስር እና አሳር ድርሻ ቀንበር ተሸካሚ ሆኖ ባለበት የዓማራ ክልል መታደግ በጦርነት ማለት ለአገር እና ህዝብ የሚኖረዉን ቦታ በብአዴን /ኢህአዴግ የስልጣን ምኞት መተካት ይሆናል ፡፡

አገር እና ህዝብ በመከራ ቋያ  እንዲነዱ የሚሆነዉ ብአዴን /ኢህአዴግን መታደግ  አስከሆነ ጦርነቱ በኢትዮጵያዉያን / ዓማራ ህዝብ እና በኢህአዴግ መካከል መሆኑን መድፈር እና ማስመር አለመቻል ችግሩንም ማድበስበስ እና ማባባስ እየሆነ እና ሊሆን ያለዉን ዉጤት ማሳነስ እና ማለባበስ ነዉ ፡፡

ህመሙን የደበቀ  መድኃኒት የለዉም  እና ህመሙ ህዝብ እና የአገር እንጂ የግል እና የቡድን ፍላጎት ማስቀጠል ጉዳይ መሆኑን በመተዉ ለሁላችን አገር እና እና ለትዉልድ የሚበጂ ከችግሩን መነሻ የሚመነጭ መፍትሄ ለማኖር ችግሩ አንኳር እንደሆነ መሰመር አለበት ፡፡

የህዝብ እና የአገር መከራ ማድበስበስ የህዝብን እንባ ማበስ የሚስችል ሳይሆን ከመከራ ወደ መከራ የሚያደርስ ለአገር መፍረስ መንስኤ እንጂ መፍትሄ ሊሆን አይችልም ፡፡

በዓማራ ክልል በጥቁር ጠበንጃ ስም የታወጀዉ የቶርነት ፍርጃ በሁሉም ረገድ ከክፍለ ግዛቱ አልፎ ለመላ አገሪቱ የሰባዊ፣ የመዋዕለ ንዋይ  እና የማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ዉጥቅንጥ እና ማጥ መግባት እንጂ ከባቢያዊም ሆነ ብሄራዊ መታደግ የሚያስገኝ አይደለም ፡፡

ብአዴን ኢህዴግን ፤ኢህዴግ ብአዴን በተለያየ ጊዜ ፣ ሁኔታ እና መልክ እርስ በርስ ተደጋግፈዉ ራሳቸዉን ለመታደግ በሚያደርጉት መለባበስ አነድም ጊዜ አገር እና ህዝብ ሲታደጉ አልታዩም ፡፡

በሁሉም ኢህአዴግን ለመታደግ በተደረጉ ጦርነቶች ትልቁን ዋጋ የከፈለዉ እና እየከፈለ ያለዉ ህዝብ እና የህዝብ ልጂ ብቻ ነበር ፤ነዉ ፡፡

አስካሁን ካለፉት የኢትዮጵያ ሶስት ዋና ዋና ጦርነቶች ኢትዮ -ኤርትራ ፣ የትህነግ የግዛት ማስፋፈት እና ወረራ  እና በዓማራ ህዝብ ላይ እየሆነ ያለዉ ጦርነት መንስዔዉም ፤ግቡም ኢህአዴግ እና የኢህዴግን ህልዉና መታደግ ነዉ ፡፡

በሰሜን ምዕራብ የኢትዮጵያ ክ/ግዛቶች -ዓማራ ክልል- የጦርነቱ መነሻ  የፖለቲካ ስልጣን ስጋት እና ስግብግብነት በጥቁር ጠበንጃ ይገባኛል በተፈጠረ አንጃ እና እንጃ የተጀመረዉ የኃይል (ጦርነት) እርምጃ የህዝቡን የአልሞት ባይ ተጋዳይ ህብረት እንዲጠናከር በማድረጉ በኃይል በህዝብ እና አገር ላይ የሚደረገዉን ዘመቻ ምንነት በግልፅ እንዲረዳ አድርጎታል፡፡ እናም ሲከር ይበጣሳል ….እንዲሉ በህዝብ እና በአገር ኪሳራ የሚተርፍ መለያየት እና ዉድቀት እንጂ መታደግ ባለመሆኑ መታደግ ለኢህአዴግ ከሆነ መጨረሻዉ እያጠፉ መኖር ነዉ ፡፡

“አንድነት ኃይል ነዉ” ፡፡

 

Allen

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

በጎጃም ለወሬ ነጋሪ ያልተረፈው ሰራዊት ! | እንደ አብይ ሰላማዊ ተቃውሞ ትግል የሚፈራ የለም!

ለነፃነት፤ ለእኩልነትና ለወንድማማችነት፤ ለሚታገሉ የለሕሊና እስረኞችና ለኢትዮጵያ ትንሳኤ ለሚዋደቁ የፋኖ ጀግኖች መታሰቢያ ትሁንልኝ ::
Next Story

ቆሜ ነው እምሞተው ( አሥራደው ከካናዳ )

Go toTop