የብርቱ ጉዳይ ጥሪ: ኑ እና ስለ አዲስ አበባችን፣ ስለ ሃገራችን ወቅታዊና መዋቅራዊ ችግሮች  እንምከር!

September 30, 2023

የፊታችን ቅዳሜ ኦክቶበር 7 ቀን በኢስተርን ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 3pm  ጀምሮ በአዲስ አበባ መዋቅራዊና ወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ ልንወያይ በጣም ሁነኛ ሁነኛ ቀጠሮ ይዘናል። በዚህ ቀን አቶ ገለታው ዘለቀ በቅርቡ ባሳተሙትና በአዲስ አበባ መዋቅራዊና ወቅታዊ ችግሮች ላይ ያተኮረውን መጽሃፍ መነሻ በማድረግ በተለይ ባላፉት አምስት አመታት አዲስ አበባን ሰቅዘው በያዙ ችግሮች ዙሪያ ጥልቅ ውይይት ይደረጋል። አዲስ አበባ የህብረታችን ተምሳሌት፣ የኢትዮጵያችን አምሳል፣ የሁላችን ዞሮ መግቢያ ቤታችንን…… ህመሟን ከውጪ ወደ ውስጥ – ከውሥጥ ወደ ውጭ እያገላበጥን እናያለን። ብሎም ደግሞ ይህቺ አብሪ ኮከብ የነጻነት ትግል ቀንዲሏን አንስታ ለራሷም ለኢትዮጵያም በሚተርፈው በነጻነት ትግል አቅጣጫዎቿ ዙሪያ አንመክርበታል። ስለሆነም ቅዳሜ ኦክቶበር ሰባት ኑ እና ስለ አዲስ አበባ በብርቱ እንምከር። በዚህ ውይይት ላይ ፖለቲከኛ  ኤንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድ፣ ዶክተር አክሎግ ቢራራ፣ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ፣ ዶክተር ሄኖክ ጋቢሳ፣ ፕሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያ፣ ዶክተር ኮነ ፍሰሃ እና ሌሎች ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና አንቂዎች ይገኛሉ፣ ሃሳብ ያካፍላሉ። ስለሆነም ቅዳሜ ኦክቶበር ሰባትን ለዚህ ታላቅ ቁም ነገር መስዋዕት ያድርጉት!

ቦታው     Emory Fellowship

6100 Georgia Ave NW Washington, DC 20011

ሰዓት ክ 3pm  ጀምሮ

ለተጨማሪ መረጃ

14134045754 ይደውሉ

የስብሰባው አዘጋጅ ኮሚቴ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የፋኖ መንፈስ በውስጡ የሌለን ደስኳሪ የአማራን ምሁር አትስሙ!

Next Story

የምዕራብ ጎጃም የፋኖ ህዝባዊ ሀይል ትልቅ ድል ፊልድ ማርሻሉን ያርበተበተ|ታላቅ ጀብድ ተፈፀመ ከግንባር የተሠሙ|ባህርዳር በላይ ዘለቀ ኤርፖርት

Go toTop