“ግርማ የሽጥላን የገደለው የአብይ አስተዳደር ነው!”- መሳይ መኮንን

April 29, 2023

ግርማ የሽጥላን የገደለው የአብይ አስተዳደር ነው! ምናልባት ዛሬ የምንሰማው ነገር ይህ መንግስት ከግድያው ጀርባ አለበት የሚለውን የአንዳንድ ወገኖች ጥርጣሬ ውድቅ እንዳናደርገው የሚከለክለን ይመስላል።

በሶስት አቅጣጫዎች በጎጃም፡ ወሎና ሰሜን ሸዋ በብዛት የገባው የመከላከያ ሀይል እንቅስቃሴ በአማራ ክልል ለሶስት ወራት የታቀደውን ዘመቻ ምክንያታዊ ለማድረግ በመንግስት በኩል የተፈጸመ ግድያ ሊሆን ይችላልም ብሎ መገመቱ ተራ ግምት አይደለም።
እነአሜሪካን ኢራቅን ለመውረር፡ አፍጋኒስታን ላይ ጦራቸውን ለማዝመት የተጠቀሟቸው ስትራቴጂዎችን ስንፈትሻቸው መንግስታት እንዲህ ያለ ሴራ ጠምቀው፡ እግራቸውን ማስገቢያ ምክንያት ሰበብ የሚሆናቸው ነገር ያደርጋሉ። የአብይ መንግስት ከአማራ ህዝብ መሳሪያ ለመንጠቅ የሚያስችለውን ዘመቻ ይከፍት ዘንድ አቶ ግርማ የሺጥላን የመስዋዕት በግ ሊያደርጋቸው እንደሚችል መጠርጠሩ ተገቢነት ያለው ጥርጣሬ ነው።
አንዳንድ የኦሮሞ ኢሊቶች በአደባባይ እንደሚናገሩትም የአማራ ክልል ትንሽ በጥበጥ ማለት እንደሚገባውና ፋኖን የመሰሉ አደረጃጀቶችን ለማፈራረስ የሆነ ትርምስ መፈጠር እንዳለበት በግልጽ ሲጽፉ አይቼአለሁ። የእነዚህ ኢሊቶች ድምዳሜ የኦሮሚያ ብልጽግና አመራሮች ጋር በስፋት እንደሚታመንበት ይታወቃል። እናም የአብይ አስተዳደር ከአቶ ግርማ የሺጥላ ግድያ ጀርባ አለ ብሎ የደመደመ ካለ ‘ጸረ ለውጥ፡ የብልጽግና ጠላት፡ ጽንፈኛና ሴረኛ’ እያልኩ አልሞልጨውም። በደንብ እሰማዋለሁ። የአብይ መግለጫ መፍጠኗም የምትጠቁመውን ነገር መዘንጋት አይገባምና

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

በአማራ ክልል ዘመቻ ተከፍቷል፥ መንግስት በይፋ ትጥቅ ለማስፈታት ለመከላከያ ስምሪት ሰጠ፥ የተወገዙት መነኮሳት ሊሾሙ ነው?!

Next Story

የ190 አማራዎችን ስልክ ተጠልፏል

Go toTop