ዳልቻ እና መጋላ – ያሬድ መኩሪያ

April 8, 2023
ሀገር ሙሉ እንክርዳድ፣ቅጥ ያጣ ቆሻሻ
እንዴት ብሎ ይለያል፣እንዴትስ ይጸዳል
ቢለቀም ቢንጓለል፣ቢበጠር ቢነፋ::
ቅርፊት ብቻ አይቶ፣ቡጡ ሳይነካ
በሰለ ይባላል ወይ፣ውስጥ ውስጡን የቦካ::
መልሰው መላልሰው፣የስህተትን መንገድ እየደጋገሙ
ማበድ ጨርቅ መጣልን ነው፣ለውጥን ማለሙ::
ዝም አይነቅዝም ብሎ፣አዋቂው ሲለጎም
ደፋርና ዐይን አውጣው፣መሪው ሆነ መቅድም::
ዳልቻ መጋላ፣መጋላ ዳልቻ የተደባለቀ
ግልጽና ቀጥታ፣አንዱን መንገድ ሳይዝ
እስከሚነቃበት፣ያው በተለመደ፣በቀየሰው ፍኖት
እያወናገረ እያወናበደ፣ትንሽ ጋት ዘለቀ::
       ~***°•***°•***~
የመሪነት የርዕዮት መንገዳቸው
ለዳመነ ለተዥጎረጎረ ቡሬ ለሆነ
ከፊት ተሰላፊዎች
መዘከርያ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ጥር ፲፮ /፳፻፲፬ ዓ.ም
January 24/2022
ሰኞ)02:44(ዊንጌት/አ.አ
©ያመጌዕ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ያማራ ፋኖ ሆይ፣ ውሻን በርግጫ መምታት እንካ ሥጋ ማለት ነው

Next Story

ኧረ ቄስ ጥሩ ሰወች ! – ቀሲስ አስተርአየ

Go toTop