የራያ አላማጣ እና ባላ ነዋሪዎች የማንነት ጥያቄያቸው ህጋዊ ምላሽ እንዲሰጠው በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ

March 19, 2023
ባሕር ዳር: መጋቢት 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) “አማራ ነን እንጅ አማራ እንሁን አላልንም፤ በጦርነቱ ወቅት በማንነታቸው ምክንያት ታፍነው የተወሰዱ ወንድሞቻችን በአስቸኳይ ይፈቱ፤ ማንነት እውነት እንጅ ፍላጎት አይደለም” የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን በማሰማት ነው የአላማጣ ከተማ፣ የራያ አላማጣ እና የራያ ባላ ነዋሪዎች የቆየ የአማራ ማንነት ጥያቄያቸው እንዲመለሥ ሰላማዊ ሰልፍ ያካሄዱት።
የፌዴራል መንግሥት በተደጋጋሚ ለጠየቁት የአማራ ማንነት ጥያቄ ሕጋዊ እውቅና እንዲሠጥ በሰላማዊ ሰልፉ ጠይቀዋል።
በማንነታችን ይደርስብን ከነበረው ግፍ ተላቀን የነጻነት አየር እንድንተነፍስ ላደረገን የጸጥታ ኀይል ምስጋና እናቀርባለን ያሉት ነዋሪዎቹ መንግሥት ለቆየ የማንነት ጥያቄያችን ሕጋዊ ምላሽ እንዲሰጠን አሁንም በአጽኖት እንጠይቃለን ብለዋል፡፡
በባለ ዓለምየ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የዚህን ሰውዬ እንጨት እንጨት የሚል ቀልድ ላለመስማት የት ልሂድ? – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

Next Story

ከንቲባዋ ዘመዶቼ ብቻ ይግቡ እያሉ ነው|”ብልጽግና ፓርቲ አሁን ላይ ትልቅ ሰው የለውም።” | የአዲስ አበባን ሕዝብ ነብር ሊያደርጉት ነው | Ethio 251

Go toTop