“እኛ ኢትዮጵያን እና ራሳችንን እንታደግ !”- ሞት ለገዳይ  !  

February 7, 2023

አንድነታችንን እና ህብረታችንን በማፅናት  ለራሳችን ነጻነት እና ለአገራችን አንድነት መቆም የዕምነት እና የኃይማኖት ብቻ ሳይሆን የመኖር አለመኖር ህልዉና ጉዳይ መሆኑን እንገንዘብ ፡፡

የቤተ ክርስቲን ግቢ እና ቅጥር ማስጠበቅ የሁሉም ዜጋ እና የሰዉ ልጆች ግዴታ ቢሆንም እንደአለመታደል የቤ/ክ ነገር የክርስቲያኖች የግል ማድረግ ስህተት ብቻ ሳይሆን ፀፀት እንዳናተርፍ እንጠንቀቅ ፡፡

ለዘመናት ዕምነትም ሆነ ማንነት ባአገር ነዉ ፡፡ አገር እንታደግ ሲባል ሁሉም ምንቸገረኝ ባይ በዛ እና አስቀድመዉ ለተገለፀላቸዉ ጀርባችንን ሠጠን ፤ አሳልፈን ሰጠን፡፡

ኢትዮጵያን ቀለሟን ወዟን  ፣ዳር ድንበሯን አጣች ፡፡ ቀጠለ ኢትዮጵያዊነት ወንጀል ሆኖ ዓማራ ብሎ ማሳደድ ….ቀጠለ ለሶስት አሰርተ ዓመታት …ይኸዉ ዛሬ ቤ/ክርስቲያን ላይ በግልፅ ከአንድ ክ/ዘመናት በላይ የተደነቀረዉ ኢትዮጵያን የማጥፋት አንዱ  ሴራ ቤ /ከርስቲያንን በይፋ መንቀፍ ፤ማነቀፍ…..በግልጥ  እየሆነ ያለዉን እያየን ነዉ ፡፡

እኛም ወገን ሆይ እናት ኢትዮጵያ ስትታመም ፤ስታዝን ፤ስትቆዝም የሚደሰት ዕኩይ እና ድዉይ ዕንጂ ሠዉ ሊሆን አይችልም እና ለሚያምኑት እና ከክርስቶስ ጋር ለሆኑት የሚያመልኩት ዓምላክ አላቸዉ ለእኛ እና ለአገራችን መዳን ህልዉና ዘብ መቆም አለብን እርሱም ጊዜዉ አሁን ነዉ ፡፡

ታላቁ መፀሃፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን “  የመዳን ጊዜ አሁን ነዉ ”እንዲል  ራሳችንን ፣ ነፃነታችንን ፣ አገራችንን ለመታደግ  በአንድነት እና በህብረት ዘብ የምንቆምበት ጊዜ አሁን ነዉ ፡፡

“በክርሰቶስ ነፃ  ወጥተናል እና ዳግም በባርነት ቀንበር ስር ላለመዉደቅ እንትጋ ፡፡”

ብረት በዕሳት …አንዲሉ በኢትዮጵያ ላይ የሚሆነዉ መከራ ሁሉ ለአለፉት ድፍን ሠላሳ ዓመታት በምድረ ኢትዮጵያ የጠፋዉን ዕዉነተኛ ኢትዮጵያዊ ዕና የነፃነት ሠዉ ለማዋለድ መሆኑን በመገንዘብ ኢትዮጵያዊነት የሚረጋገጥበት የመከራ ጠርዝ ላይ መገኘታችን የመከራ ብዛት ሊያበረታን እንጂ ተስፋ ሊያስቆርጠን አይገባም ፡፡

“አንድ ኢትዮጵያ ፣አንድ አገር ፣ አንድ ህዝብ ፡፡”

ሞት ለገዳይ  !

Allen Amber

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የተጠያቂነት  ያለህ አገር  መፍረሱ ነው – ሰመረ አለሙ

Next Story

“ተጠጋ ወደ እሳቱ” አገር ሳያጠፋ በቅጠል

Go toTop