የናዚሥቶቹ የመቀበሪያ ቀን ቅርብ ነው “በሰፈርከው  ቁና ይሰፈርልሃል“ ከአባታጠቅ ምንዳሁነኝ

December 8, 2022

ሹፌሩ ሳያውቅ መሪው መዞር አይችልም ። አውቶማቲክ እና እጅግ ዘመናዊ መኪና እንኳን በመጀመሪያ በተቀነባበረለት ፕሮግራም መሠረት እንጂ በደመ ነፍስ አይጓዝም ። አንድ የአገር መንግሥትም የጠራ እና ዜጎችን ያቀፈ የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ መንገድ ይኖረዋል ። ፕሮግራም ና ፖሊሲ ይባላል ። በወጉ በተሰነዱ ፣ ፖሊሲዎቹና ፕሮግራሟች ነው ፤ መንግሥት አገርን የሚያሥተዳድረው ። ህዝብንም የሚመረው ። ህዝብንም ይህንን በመረዳት ነው ከጎኑ የሚሰለፈው ።  ወዴት እንደሚወሥድህ ከፖሊሲው አንፃር እያወቅህ “ አንድ የጋራ ማህበረሰብ መፍጠር “ ይቅር እና ሥልጣን አገርቶ ሥልጣኑንን በኃይል የቀማውን ክልል መቆጣጠር ሲያቅጠው ዜጋ  ምን ይላል ?

የብልፅግና መንግሥት አሪፍ አሪፍ የኢኮኖሚ ፣የውጪ ጉዳይ ፣ የግብርና ፣የከተማና የገጠር የተለያዩ ፖሊሲዎች ፣ እና የሚኒሥትር መሥሪያ ቤቶች ደንብና መመሪያዎች እንዳሉት ዜጎች ያውቃሉ ።

( ይኼ የጠላቶቻችንን ኦሮሞ ፣ አማራ፣ትግሬ እያሉ መከፋፈል ወዲያ አሽቀንጥረህ ጣለው ። በኢትዮጵያ ሉአላዊ ግዛት ያለው የማይበላለጥ ዜጋ ነው ።  ኢትዮጵያዊ ዘጋ ። የሰው ስብስብ ። …)

እርግጥ መንግሥት   የሌለው የክልሎች  የፖለቲካ አካሄድን መቆጣጠሪያ መንገድ ነው ። ይህ መንገድ ለፊደራል መንግሥት በግልፅ አልተሠናደለትም ። የለውም ማለትም ይቻላል ።  የፊደራሉ መንግሥት በእነዚህ  ክልሎች ፣ ፖሊሲዎቼን ላንሸራሽር ካለ  የሚያንሽራሽረው ሃሳብ መሪ  አልቦ  ነው ። እናም በዕውር ድንብሩ  ሲያሽከረክር ገደል ቢገባ አይገርምም ።

ዳር ሆነን እንደምንታዘበው ፣ ለመንግሥት  የተቀናጀ እና   ተመሳሳይ የሆነ የቅጥፈት ሪፖርት በየጊዜው ይደርሰዋል ። የፀጥታና የሠላም መሥፈን ሪፖርትም ለፊደራሉ መንግሥት በየቀኑ ይላክለታል ። የፊደራል መንግሥቱም አገር ሠላም ነው ብሎ የልማት ሥራ ላይ ያተኩራል ። የሚሠራው ትሪሊዮን የወጣባቸው ሥራዎች ግን እንዲወድሙ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ትሪሊዮን ዶላር በየክልሉ  ለግጭትና ለሽብር እየበተኑ ነው ። በየክልሉ የሚደረገውን ለመቆጣጠር የሚያሥችል መንገድ የፊደራል መንግሥቱ የለውም ። ያለመንገድ ሃሳቡን ለማንሸራሸር እንዴት ይችላል ? መሪው ለአገር እና ለህዝብ  ጠቃሚ ሃሳቡን እንዴት ማስረፅ ይችላል ?

የውጪ ጠላቶቻችን ግን መንገድና መሪ በየክልሉ አላቸው ። በመሪዎቻቸው ተጠቅመውም ፣ በጊዜ የተቀመረ ፣ በቦታ እና በሁኔታ የታጀበ ሽብር እና ቀውስ ለመፍጠር ሌት ተቀን በሚሥጢር ይሰራሉ ። ሃሳባቸውንም ያሰርፃሉ ። ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች በመንግሥት   አፍንጫ ሥር በመሪያቸው ተጠቅመው ቀየቀኑ  እሣት ይጭራሉ ። የሚሪው ተላላኪ ወጣትም ረብጣ ብር ተሰጥቶታል እና ሌላው ተማሪ ተማረ አልተማረ ደንታ ቢሥ ነው ። በአዲስ አበባ ፖሊሥም ውሥጥ የግብፅ ተከፋይ ፖሊሶች እንደተሰገሰጉ ከኑሮቸው አንፃር መጠርጠር ይቻላል ። በአዲሥ አበባ ዙሪያ ለመመደብ አንድ የኦሮሚያ ፖሊሥ 50 ሺ ብር ይከፍላል ። ይባላል ። ለኃላፊው ። ለአዘዋዋሪው ። ገንዘቡን ግነ ኬት ያመጣል ?

እንግዲህ እነዚህ ናቸው  ያልሆነ የውሸት መረጃ ለአብይ ሹክ የሚሉት ። በሃሰት ፈጠራ ያናድዱታል ። ብሬን ወሽ ያደርጋሉ ። የዜግነት ነፃነትን የሚጋፉ ማአት ያበዱ ፖሊሶች በከፍተኛ አመራር ላይ እንደተቀመጡ ማወቂያ መንገዱን ይዘጉበታል ። እናም ከአራጆቹ ጋር በፀጥታ ይጓዛል ።

ዜጋ ግን ያውቃል ። ሥለ  አገር እንጂ ሥለ እና ሃያቶላ ደንታ የለውም ።

ዶ/ ር አብይ አህመድ እንደ አገር መሪነታቸው ሥለ አገር እንጂ ሥለ ጠባብ እብድ የፖለቲካ ሰዎች እና ሥለባንዲራቸው የሚጨነቁበት ጊዜ ያለፈ መሆኑንን ዛሬ  የሚገነዘቡ ይመሥለኛል ። ….

አሜሪካ እንደ ቀድሞዋ ሶቬት ህብረት  ኢትዮጵያን ለመከፋፈል  እንደ ጎርቫቾቭ ዶ/ር አብይን ትጠቀማለች ብዬ ማሰብ እጅግ ይከብደኛል ። ይሁን እንጂ ሱሉልታ ኦነግ ሸኔ ቀረጥ ከሰበሰበ የአሜሪካ ዕቅድ እየተሳከ ነው ማለት እችላለሁ ። …

መንግሥት  ፣ ማወቅ ያለበት “  ከአንተ በፊት እኔን ያሥቀደመኝ ። “  በማለት “ በፉገራ “ የተካኑ ተልከሲሶች  ከፍትህ እያራቁት ነው ። ከሴትና ከሥጋ ውጪ የማይታያቸው  ቱባ ባለሥልጣኖች በየክልሉ እና ከአጠገቡ ተቀምጠዋል ። የ 1 % ቱ ጥጋብ የጠቅላለው ደሃ ህዝብ ( የ99% ) የሚመሥላቸው ትላንትን የረሱ ግብዞች መዓት ናቸው ።…

ለእነሱ ፣ አንድ ታላቅ አገርን ማሥተዳደር ማለት ፊውዳልና መኳንንት መሆን ማለት ነው ። በየቀኑ አሥረሽ ምቺው ማለትን ለምደዋል  ። በየቀኑ ለህዝብ ሠላም እና ደህንነት መጠበቅ ብሎ የሚሰዋው የመከላከያ ኃይል ፣ የፊደራል ፖሊሥ እና የየክልሉ ልዩ ፖሊሥ ከቶም አይቆጫቸውም ።

እንዴ ! እነዚህ ሰዎች ከደረግ በባሰ አብዮት መጥፋትን  ይፈልጋሉ እንዴ ? ማንም ይሁን ማን ሊተርፍ የማይችልበት አብዮት ፀጥ ባለው ፤ ከጠባብ የኦሮሞ ፖለታከኞች ውጪ ባለው ፤ ፖለቲከኛ እና ህዝብ ነገ የሚከሰትበትን መንገድ እነ “ የግብፅ ጉዳይ አሥፈፃሚዎች  “ እየጠረጉ ነው ።  ነገ በአሰቃቂ መልኩ  በራሳቸው ላይ ሰቆቃ  እንደሚመጣ ግን የተገነዘቡ አይመሥልም ። እየታረደ ዝም የሚል ፍጡር የለም  ። …

ከሀገር የሚበልጥ የለም ። ዛሬ ያለመሪ በየክልሉ  እየተጓዘ ያለው የፊደራሉ   መንግሥት ፣ ነገ የአንድ ዘመናዊ ሉአላዊ መንግሥት ትክክለኛው አቅጣጫ ፣ ዜግነት ተከብሮ በዜጎች ቅቡል ሃሳብ መመራት እንጂ የ18 ክ/ዘ ኋላ ቀር አሥተሣሠብ መዘመር  እንደማያዋጣ እንደሚገነዘብ አሥባለሁ ። መሪው በአጠቃላዩ ዜጋ ሃሳብ እና ፈቃድ  መጓዝ ማምን ሲጀምር ፣ ሁሉም “ ናዚስቶች “ ፣ በሰፈሩት ቁና   ይሰፈርላቸዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ጅልና ብሔረተኛ አትሁን፤ ዜጋ ሁን!! በፍሬሕይወት ተሰማ

የአቢይ አህመድ ጨለማ ጉዞ!
Next Story

አዶልፍ ሂትለርና ይሁዶች፣ ጭራቅ አሕመድና አማሮች – መስፍን አረጋ

Go toTop