ኦነግ ሸኔ ብሎ ነገር የለም … ያለው የፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ፕላን ቢ  እና ሲ ነው… – ሲና ዘ ሙሴ

November 12, 2022

ኦነግ ሸኔ ብሎ ነገር የለም ። ያለው ሥለ ገንዘብ ብሎ ሰው የሚያርድ የአውሬ ስብስብ ነው ። ያለው በግፍ በጭካኔ እና በስርቆት ሥለሚሰበሰብ ሀብት እና ንብረት የሚጨነቅ የአውሬ መንጋ ነው ። ያለው እየተዘረፈ ሥለሚበላ ሥጋ  ብቻ የሚያሥብ ለሆድ ብቻ የሚኖር ከአውሬና ከእንስሳ ጎራ የሚመደብ ፀረ ሰው ፣ ፀረ ህብረተሰብ ፣ ፀረ አገርና ትውልድ ” በለዔ ሰብ  ” ቡድን ነው ።

ይህንን ፀረ ሰው እና አገር አፍራሽ ” በላዔ ሰብ እና መንጋ ቡድን ” መሐል ከተማ ሆነው ( በመላው አትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ውሥጥ ሆነው ) የሚመሩትና የሚደግፉትም ትላንት ምንም የሌላቸው ዛሬ በለባንክና ባለፎቅ የሆኑ ግለሰቦች ናቸው ። እነዚህ ግለሰቦች  ከግብፅ ፕላን ቢ ጋር በመቀናጀትም  ” የአሸባሪ ተግባር በመፈፀም የኢትዮጵያን ህዝብና መንግሥት እንዳይረጋጉ ማድረግ ። ” የሚለውን ዕቅድ በማስፈፀም ላይ ናቸው   ። ትላንት በአረብ በረሐዎች አይሲስ አንገት ይቀላ ነበር ። ዛሬ ደግሞ በኦሮሞ ሥም ተደራጅቶ አንገት የሚቀላ የግብፅ ተላላኪ  አውሬ ቡድን  ፈጥረወልናል ።

ምናልባትም የሰውን  አንገት ማረድ እንዴት ቀላላ እንደሆነ የሚያሰለጥን ሤጣን በከፍተኛ ብር ክፍያ ከዚህ ኦነግ ሸኔ ተብዬ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ እና የሽብር ቡድን ጋር እንዳለም ጠርጥሩ ። ትላንት በህውሃት ቤት ነበረ ። ዛሬ ደግሞ በኦነግ ሸኔ ተብየው ቤት ሥለታም ቢላውን ከፍ አድረጎ ይዞ እብድ እብድ እየተጫወተ ነው ። ይህንን የእብድ ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም  ያላሰለሰ ድጋፍ የሚያደርጉለት የጥቅም ተጋሪዎቹ በመንግሥት ማዋቅር ውሥጥ የተሰገሰጉ ምናልባትም ከፍተኛ አመራራ የሆኑ ሆዳም ግለሰቦች ሊሆኑ እንደሚችሉ ህዝብ ከጠረጠረ ቆየ ። ለዚህ ዋቢ የሚሆነን ደግሞ በኃቅ ህዝብን የሚያገለግሉ የኦሮሚያ ክልል አመራሮች  በእነዚህ አውሬዎች በግፍ ና በጭካኔ  መገደላቸው ብቻ ሳይሆን ፣ አያሌ የኦሮሚያ ፖሊሶች እና ልዩ ኃይሎች ለግዳጅ መሰማራታቸው አሥቀድሞ ለአውሬው እየተነገረ በአሳዛኝ ሁኔታ በጉዞ ላይ ሳሉ በድንገተኛ ጥቃት ማለቃቸው ነው ። ይህ የሚያሥረዳን ” ኦነግ ሸኔ ” የተሰኘ ቡድን ያለመኖሩን ነው ። ያለው ከላ እስከታች በኔት ዎርክ የተደራጀ ፣ አገር አፍራሽ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ አውሬ ቡድን ነው ። ይኽ ቡድን ለዘረፋ ፣ በጭካኔ ለማረድ እና ለመግደል በጠላቶቻችን የተፈጠረ ሆኖም ሆዳም እና ህሊና ቢሥ ምሁራን ፣ ትልቅ የሚባሉ ግን ″ የትኋን አሥተሳሰብ ያላቸው  ″ ፖለቲከኞች እና ባለሥልጣናት ፣ በብርቱ የሚደግፉት በመሆኑ መሐል አገር ድረስ ዘልቆ የጭካኔ ተግባር ይፈፅማል ።ይኽንን እኩይና ኩንን ተግባር በግልፅ እና በአደባባይ በፀሐይ ብርሀን ሲፈፅምም   ሃይ የሚለው የጠፈውም በዚህ ምክንያት ነው ።  የግል ሀብታቸውን እያደራጁ፣ ዶላራቸውን በውጪ እያሳበጡ  እና እጅግ የተቀናጣ ኑሮ በሸገር እየኖሩ እንዴት ብለው ከጠላቶቻችን የሚያገኙትን ገንዘብ ከላዩ ላይ እየቆነጠሩ   በመሥጠት  ፣ ለዚህ ያበቁትን እና እነሱን ቱጃር ያደረጋቸውን የአውሬ ቡድን እንዴት ተው ! ይበቃል ! እረፍ ! ሰውን በመግደል እንደ አውሬ  መኖርህ ይብቃ   ሰው ሁን ! ይሉታል ። መጀመሪያ ራሳቸው ሰው ሳይሆኑ ሌላውን አውሬ አምሳያቸውን ወደ ሰው ለመቀየር እንዴትስ ይችላሉ ?

በነገራችን ላይ የፌደራል መንግሥቱ  በፀጥታ ኃይሉ ውሥጥ የተሰገሰጉ በመጥፎ ሱስ የተበከሉ ፣ ለሱሳቸው ሲሉ አገር ከመሸጥ ወደኋላ የማይሉ  በፀጥታ አካላቱ ውስጥ ያሉ  አባላቱን ለማጥረት ፣ ልዩ ኦፕሬሽን ወይም የማጋለጫ ውይይት ″ በጎድ ደረጃ ″ ሳይዘገይ ማካሄድ እንዳለበት አስባለሁ  ። የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ ወታደራዊ ዲሲፕሊኑ ከብረት የጠነከረ መሆን ይገባዋልም ። እንደ ብረት የጠነከረ ዳሲፕሊን ላለው የመከላከያ ሠራዊትም ኢትዮጵያ ከማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ  የተሻለ ደመወዝ ልትከፍለውና  ልትንከባከበውም እንደሚገባም አምናለሁ ። የአገር ሠላም ዋሥትና የመከላከያ ሠራዊቱ ፣ የፊደራል ፖሊሱ እንዲሁም በየክልሉ ያሉ ኃቀኛ ፖሊሶች እንደሆነም አበክረን መረዳት ይኖርብናል ። በእነዚህ ህግ አሥከባሪ ፣ አገርና ህዝብን ጠባቂ ተቋሞችም  ውሥጥ ያለው ″ ንቅዘት ″ እሥካልተወገደ ድረሥ የኢትዮጵያ ሠላም አሥተማማኝ አይሆንም ።

ትላንት ፣ የህውሃት ጀነራሎች የግል መኖሪያ ቪላ ብቻ  ቢሰሩ ኖሮ አይገርመንም ነበር ። የንግድ ፎቅ ሠርተው ሲያከራዩ ግን አይተናል ። ይህ ምን ማለት ነው ? ይህንን የሚሰማ በዝቅተኛው እና በመካከለኛው አመራርና በተራ ወታደርነት ያለው በደመወዙ ብቻ የሚተዳደረው ፣ ከዓመት እሥከዓመት ኑሮው ባለበት የሚረግጠው ዓባል ምን ይሰማዋል ?  በእውነቱ ወደ ታችኛው እና የበዛ መሰዋትነት ወደ ሚከፍለው ለውይይት ስትሄድ ውድ ኮትህን ወደ ርካሽ \ ጃኬት መቀየሩ ከቶ ምንም ዋጋ እንደማይኖረው መገንዘብ አለብህ ። መጀመሪያ እራስህ በእውነት ከሥግብግብነት እንደተላቀቅህ ራስህን ጠይቅ ። ሥግብግብ ሰው ህሊና ቢሥ ነው ። ማሥተዋልም ከቶም አይችልም እና ይህንን ፍራ ፡፡ …

ዛሬ ፣ ዛሬ ሥግብግቦች አና ከራስ በላይ ነፋስ ባዮች በመንግሥት ማዋቅር በከፍተኛው አመራር ውሥጥ በመብዛታቸው ነው ፣ ተራ ነፍሰ ገዳይ አውሬዎችን እንኳን ማጥፋት ያልተቻለው ። ከተማ ሲገቡ ድምፅን አጥፍቶ በመመሸግ እምሽክ ማረግ ሲቻል ፤ ” እኛ በዚህ ሥፍራ ተሰባሥበን ቁጭ እንላለን እናንተ ገብታችሁ ዝረፉ ። ” በማለት ይመስላል ወደ ወለጋ ከተሞች እየግቡ ያለፍርሃት ዘርፈው ወደ ጨካቸው የሚመለሱት ። አሥቀድሞ ይህ ከፍተኛ ባለሥልጣን ( ወታደራዊም ሆነ ሲቪል )ከአውሬዎቹ ሥንት ሚሊዮን ብር ቢቀበል ነው ፣የፀጥታ መዋቅሩን ″ አርፈህ ቁጭ በል ። ″ ብሎ ቀጭን ትዕዛዝ የሚሰጠው ?  በዚህ ዓለም እኮ  ለፅድቅ ተብሎ ዘረፋ ፣ ግድያ እና ሰው ማረድ ይከናወናል እንዴ ?! …

በዚህ ዓለም ላይ፣  ሁሉም ጦርነት ለጥቅም ሥለ ጥቅም ነው  የሚከናወነው ። ጥቅምህን ሲያሳጡህ ጦርነት ትከፍታለህ ። ያልተገባህን ሆኖም የቋመጥክበትን ጥቅም ለማግኘት ጦርነት ተከፍታለህ ወይም ታሥከፍታለህ ። እንዲህ ዓይነቱ ጠርነት ነው ፣ ዛሬ በዓለማችን እየተከናወነ ያለው  ።  በእኛ አገርም እንዲሁ ።

ኦነግ ሸኔ የሚባል የሌለ የሽፋን  ሥም ይዘው ፣ በባርነት ያልተያዘውን የኦሮሞ ማህበረሰብ ነጻ እናወጣለን በማለት አላማቸውን የማይደገፈውን ሁሉ ፣ ቋንቋ እና ጎሳ ሳያመርጡ   ጦርነት ከፍተውበት ፣ ጭካኔ በተሞላ መንገድ የሚገድሉ ፣ የአውሬ ሥብሥቦች ፣ በአገር ውሥጥ ያሉ ትሆን ፐለቲከኞችን ወደሥልጣን ለማምጣት አንደሆነ ግን መታወቅ አለበት ። እነዚህ ትሆን ፖለቲከኞች ፓርቲ መስርተው በሰላማዊ መንገድ እንቀሳቀሳለን የሚሉ አስመሳዮች ናቸው ፡፡  በውጪ   ፀረ ኢትዮጵያ ጠላቶቻችን በገንዘብ እንደሚደገፉ የታወቀ ነው ። በእርግጥ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች የቋመጡለትን ጥቅም ለማግኘት የሚችሉት ኢትዮጵያን  በማፍረሥ  ነው ። ( አንባቢ ሆይ ልብ በል ፤ እንደ ቴዎድሮስ ጸጋዬ አይነቱን ልበ እውር ፣ በገንዘብ ቀጥረው የጥላቻ ጥሩንባ ቢያስነፉ አይገርምህ ) ።

ዛሬ የኢትዮጵያ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማፍረስ በፕላን ቢ እየተንቀሳቀሱ ነው ። ፐላን ሲም አላቸው ፡፡ ያንን በጊዜው እገልፅዋለሁ ። ጅማሬው ግን  ሀ ተብሏል ።  ለጊዜው ዛሬ ፣ ለዕቅዶቻቸው ግብ  ያቋቋሙት ፀረ ሰው የአውሬዎች ሥብሥብ በሙሉ ኃይሉ ፣  ሌት እና ቀን  ለጥፋት ተግባር እየተንቀሳቀሰ ነው ። ይህንንም እውነት ለመገንዘብ  ከፈለክ አፍንጫህ  ሥር  ምሥረቅ እና ምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ የሚታረዱትን ንፁሐን ተመልከት  ።  የዚህ አሸባሪ፣ አፍራሽ እና አውዳሚ አውሬ ቡድን ሞተር  ከአዲስ አበባ እስካልጠፋ ጊዜ ድረስም የዘረኛ አክራሪዎች ፕላን ቢ እና ሲ ይቀጥላል ። …

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ፍትህ የሌለው እርቅ አሁንም የሞተ ነው! – በላይነህ አባተ

Next Story

የኤፍሬም ማዴቦ ሸፍጥ፤ ያይጥ ምስክሯ ድንቢጥ (ክፍል 2) – መስፍን አረጋ

Go toTop