ወደ አዲስ አበባ የመግባት መብታችን ይከበር!    ሁለተኛ ቀን ደጅ ጥናት

September 30, 2022
ትናንትና እንዳጫወትኳችሁ አዲስ አበባ አትገቡም ተብለን ወደ ደብረ ብርሃን ከተመለስን በኋላ የዞኑ አስተዳደር ቢሮ መላ ይፈልግልን ስንል ደጅ ጥናት አምሽተን ምንም መፍትሄ ሳናገኝ ተበታትነን አደርን።
ዛሬ ጠዋት ማለዳ ላይ ቁጥሩ አያሌ የሆነ ህዝብ የሰሜን ሸዋ ዞን ፅህፈት ቤት ደጃፍ ላይ ተሰብስቦ እንደገና ደጅ ሲጠና ነበር። ይሁን እንጂ ያነጋገርናቸው ባለስልጣናት ነገሮች ከአቅማቸው በላይ እንደሆነ ገልፀዋል። ይሁን እንጂ ህዝቡ በእንባና በቁጣ ቁጭቱን ገልጿል። ዛሬስ እንዴት አማራ የሚቆረቆርለትና መከታ የሚሆነው መሪ አጣ የሚለው ድምፅ ከፍ ብሎ ሲሰማ ነበር።
ብዙዎቹ የአዱስ አበባን መታወቂያ ለባለስልጣናት እያሳዩ የደረሰባቸውን በደል ቢገልፁም ያገኙት አንዳች መፍትሄ የለም። ሌላው ቀርቶ ከነዚህ ተጓዦች መሃል ምንም ቤሳቤስቲ የሌላቸውን ማረፊያ ፈልጉላቸው የሚሉ ድምፆች ቢሰሙም ዘወር ብሎ የሚያይ መሪ ጠፋ።
ይሁን እንጂ አንዳንድ እመጫቶችና ልጃገረዶች የሚያርፉበትን ቦታ ስናፈላልግ የቁልቢ ፔንስዮን ባለቤት አልጋና ተፈላጊ ነገሮችን ለማሟላት ቃል ገብተው እነሆ የተወሰኑ ወገኖች በዚያ አርፈዋል። በዚህ አጋጣሚ ከዚህ ፔንስዮን ባለቤት ጋር ያስተዋወቀኝና እህቶቻችን ማረፊያ እንዲያገኙ ምክንያት ለሆነው ወንድም ምስጋናዮ ከፍ ያለ ነው።
 ሌሎቹን ብዙ ወገኖች እንግዳ ተቀባይ የሆነው የደብረ ብርሃን ህዝብ በአንድም በሌላም መንገድ ረድቶልናልና እግዚአብሔር ይባርክልን።
አሁንም መቼ ወደ አዲስ አበባ መግባት እንደምንችል አናውቅም። እዚሁ ሆነን ሁኔታውን እየተከታተልን ነው። ዛሬ በነበረን ስብሰባ ላይ ብዙዎች መራራ እንባ ሲያነቡ ማየት ምንኛ ልብ ይሰብራል። አማራ በእውነት ለመብቱ የሚታገሉ መሪዎችን ያላገኘ ህዝብ ነው። ያሳዝናል።
ገለታው ዘለቀ
ደብረብርሃን

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ዒላማውን የሳተ የፖለቲካ ትግል ድግግሞሽ እና ውጤቱ – ጠገናው ጎሹ

የአቢይ አህመድ ጨለማ ጉዞ!
Next Story

የኦነግ/ኦህዲዶች አይኪው ቢለካ … ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

Go toTop