እኔዎች (እኔያት) – በላቸው ገላሁን

September 21, 2022

እኔዎች (እኔያት)

አንዱ እኔ ሲጠራኝ

አንዱ እኔ ሲልከኝ

ሌላው እኔ ሲጥለኝ

አንዱ እኔ ሲያነሳኝ፣

አንዱ ወደ ግራ

ያአንዱ ባለጋራ

አንዱ ወደ ደጅ

የሌላው ወዳጅ፣

ሌላኛው ወደ ቀኝ

ሌሎቹን እንዲዳኝ

አንደኛው ወደ ታች

ለራሱ ሊያመቻች፣

አንዱ ወደ ላይ

ሊነካ ሰማይ

አንደኛው ወደ ፊት

ሌሎቹ እንዳይቀድሙት

አንዱ ወደ ኋላ

ሊያጣራ ሊያብላላ፤

አቤት የእኔ መዓት የራሴ ብዛቱ

ለየቱ እንቢ ብዬ ልታዘዝ ለየቱ?

እኒህ ሁሉ እኔዎች ውስጤ ተከምረው

ሁሌ እየተጣሉ አልስማማ ብለው

አንድ እኔ ባተለ ፍዳውን ቆጠረ

ሌላው ኔ ደስ ብሎት ተኝቶ እያደረ።

                 በላቸው ገላሁን (ነሓሴ 1998)

                 (USA)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የሎንደኖቹ ጥቂት የዲያስፖራ ይሁዳዎችና ዘራፊዎች ቅሌት!! (ተዘራ አሰጉ ከምድረ እንግሊዝ)

Next Story

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚያካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የ541 ሚሊዮን ብር የበጀት ጥያቄ አቀረበ

Go toTop