![](http://amharic-zehabesha.com/wp-content/uploads/2022/09/307018897_2740366432763845_6416153616472997589_n.jpg)
የፍትህ ቢሮው የሙስና ወንጀሉን ማጣራት ከመጀመሩ በፊት አቶ ሰማ ተምሮበታል ከተባለው የቻይና ዩንቨርስቲ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኤንድ ኢኮኖሚክስ ተምሮ የተሠጠው የ(PHD) የምስክር ወረቀት ካለ በኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የአቻ ግምቱን በማሠራት እስከ መስከረም 12/01/2015 ዓ/ም ማስረጃውን ለሶስት ተቋማት እንዲያስገባ አዝዟል።
በዚህም አንደኛ ለክልሉ ፍትሕ ቢሮው፣ ሁለተኛ ለክልሉ ሲቪል ሠርቪስ ኮሚሽን፣ ሦስተኛ ለክልሉ የብልፅግና ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ማረጃውን የማያቀርብ ከሆነ ምርመራ ማጣራት እንደሚጀምር ማስታወቁ ተሠምቷል።
ይህንን የሠሙ የትምህርት ማስረጃ ያጭበረበሩ ሌሎች ባለ ስልጣናት ጭምር ጭንቅ ውስጥ መግባታቸው ታውቋል።