ልዩ መልዕክተኞቹና አምባሳደሮቹ ለሰላም ንግግሮች ጥረት ከማድረግ ይልቅ በሌላው ወገን የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ላይ ተጠምደዋል ሲሉ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ

August 5, 2022

ወደ መቀሌ አቅንተው የተመለሱት ልዩ መልዕክተኞችና አምባሳደሮች ለሰላም ንግግሮች ጥረት ከማድረግ ይልቅ በሌላው ወገን የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ላይ መጠመዳቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ልዩ መልዕክተኞቹና አምባሳደሮቹ ጉዳዩን የያዙበትና ያዩበት ሂደት ተገቢነት እንደሌለው በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ወደ መቀሌ የተጓዙት ልዩ መልዕክተኞቹና አምባሳደሮቹ ለሰላም ንግግሮች በማያሻማ መልኩ ቁርጠኝነት እንዲኖር ጫና ከማድረግ ይልቅ፤ በሌላው ወገን የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ላይ መጠመዳቸውን ተናግረዋል።

ተቋርጠው የሚገኙ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ወደነበረበት መመለስን በተመለከተ የመንግስት ፍላጎት ግልጽ ነው ያሉት አምባሳደሩ፤ የሰላም ንግግሮችን ለማስጀመር የሚቻልባቸው ጉዳዮች ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል ሲሉም ገልጸዋል።

ልዑኩ ከሰላም ንግግሮች ላይ ከማተኮር ይልቅ ከመቀሌ መልስ ባወጣው መግለጫ ረጅም ርቀት የተሄደበትን እና መልስ የተሰጠበትን ወደ ትግራይ ክልል ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ የማቅረብ ጉዳይ መልሶ ማንሳቱን አምባሳደር ሬድዋን አንስተዋል።

ወደ ክልሉ ርዳታ በስፋት እየቀረበ ስለመሆኑ የአውሮፕላን በረራም ያለምንም ገደብ ስለመፈቀዱ የነዳጅ ጉዳይም መፍትሄ የተሰጠውና በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ መሆኑን አምባሳደሩ በመልዕክታቸውገልጸዋል።

በድጋሚ መታወቀ ያለበት የሰላም ንግግሩ የሚመራው በአፍሪካ ኅብረት ብቻ ነው ሲሉም ነው አምባሳደር ሬድዋን ያስታወቁት።

(ኢ ፕ ድ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ግስላው የአማራ ልዩ ኮማንዶ በዛሬው ዕለት ተመርቆ በማየቴ ደስ ብሎኛል! – ~ አሸናፊ ገናን

Next Story

መንጠራራትና ሀሰታዊ ትርከት አዋቂነትን አያላብስም!! (አኒስ አብዱላሂ)

Go toTop