በአፋር ክልል ሰርዶ ኬላ ጣቢያ በተደረገ ፍተሻ ወደ ትግራይ ክልል አስቸኳይ ድጋፍ እና የሕክምና ግብአቶችን በጫነ ተሽከርካሪ ውስጥ ገንዘብ እና ፈቃድ ያላገኙ እቃዎች ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ሊዘዋወር ሲል መያዙን ገልጿል።
ድርጊቱን የፈጸመው አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር መዋሉንና ተሽከርካሪው ኮሚቴው ከአንድ የንግድ ኩባንያ ለአጭር ጊዜ በኪራይ የወሰደው መሆኑን አመልክቷል።
የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ “ከተገኘው ገንዘብ እና እቃዎች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለኝም ድርጊቱን አጥብቄ አወግዛለሁ” ብሏል በመግለጫው።
ኮሚቴው “በመላው ኢትዮጵያ በትጥቅ ግጭት እና ሌሎች ሁከቶች” የተጎዱ ሰዎችን ብቻ መርዳት የሚፈልግ የሰብአዊ ድርጅት እንደሆነና በኪራይ ያመጣው ከባድ የመኪና አሽከርካሪ ያጋጠመው ሁኔታ በስራው ላይ ተጽእኖ እንዳያሳድር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
በአፋር ክልል ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ቅርንጫፍ ዱብቲ ወረዳ ሰርዶ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ8 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ እና የተለያዩ ያልተፈቀዱ ቁሳቁሶችን መያዙ ይታወቃል።
ኢዜአ)