ሮብ ሰኔ 8 ፣ 2014 ዓ/ም
አዲስ አበባ
- ለክቡር ጠ.ሚኒስትር ዶ.ር አቢይ አህምድ ዓሊ_3.Mon. 20 June 2022-13.10.14 (1)
- .-ለክቡር-ጠ.ሚኒስትር-ዶ.ር-አቢይ-አህምድ-ዓሊ_2.Mon_.-23-May-2022-15.9.14-1
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት (በኢ-ሜይል“info@pmo.gov.et”)
- ለክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ዓሊ
- ለቅሬታና አቤቱታ ጽ.ቤት/ ክፍል
በተከበረው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት
- ለአፈ-ጉባኤው/ ለአፈ-ጉባኤው ጽ/ቤት
- ለሕግ፣ ፍትሕና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
- ለዋናስራ አስፈጻሚ፡- አቶ ረሻድ ከማል፣
- ለቤቶችአስተዳደር ዘርፍ ም/ስራ አስፈጻሚ፡- አቶ ይርጋለም ኩመሊት፣
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- (1) የፌ.ቤ.ኮ ላከን ባሉ የቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤትና በፖሊስ ሃይል በዛሬው እለት ከምኖርበት አፓርታማ እንድወጣ ስለተደረግኩኝ ይኸው ሁኔታ ወድያውኑ/ ዛሬውኑ በአስቸኳይ ተስተካክሎ ወደነበርኩበት አፓርታማ ቤቴ እንድመለስ እንዲደረግ መጠየቅ፣
(2) በወረፋየ መሰረት የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አፓርታማ ቤት በስሜ እንዲደረግልኝ አሁንም እንደገና ደጋግሜ ስለመጠየቅ፣
ለበርካታ ዓመታት እየኖርኩበት ያለሁት አፓርታማ ቤቴ ችግር በተመለከተ ከአሁን በፊት የጻፍኩላችሁ ተደጋጋሚ ማመልከቻዎች የሚታወሱ ሆነው በተለይም ሚያዝያ 5 2014 ዓ/ም በግልባጭና ግንቦት 15 2014 ዓ/ም በአድራሻ “በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት (በኢሜይልinfo@pmo.gov.et– ለክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ዓሊና ለቅሬታና አቤቱታ ጽ.ቤት/ ክፍል እንዲሁም በተከበረው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለሕግ፣ ፍትሕና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ” ለጻፍኳቸው ማመልከቻዎች ፍትሃዊ መልስ በመጠባበቅ ላይ እያለሁ በማይጠበቅ ፍጹም ማንአለብኝነት፣ አምባገነናዊነትና፣ ጨካኝ አረመንያዊ፣ ሰይጣናዊ/ጋኔናዊና ኢሰብአዊ በሆነ ኢፍትሃዊ ውሳኔ ምክንያት በፖሊስ ሃይል ጭምር ዛሬ ሰኔ 8፣ 2014 ዓ/ም እኩለ ቀን አከባቢ ለበርካታ ዓመታት ከኖርኩበትና አገር ሰላም ነው ብይ ከተቀመጥኩበት የመኖሪያ አፓርትመንት ቤቴ እንድወጣ በመደረጌ ለከፍተኛ ችግር ተዳርጌ እገኛለሁ፡፡
ስለዚህ ይህ ሁኔታ በአስቸኳይ ዛሬውኑ ተስተካክሎ ወደ መኖሪያ ቤቴ እንድመለስ አሁንም በትህትና እያመለከትኩኝ ይህ ባይሆን ግን ህግና ህግ አስከባሪ ባለበት አገር ውስጥ እንዲህ ዓይነቱ የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ መሆኑ የሚነገርለት የአገሪቱ ህገመንግስትንና የአገሪቱ ህጎችን በመጣስ ዘግናኝ የህገ መንግስታዊና ሰብአዊ መብቴ መረገጥ ለማስተካከል ብቻ ሳይሆን እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ያለኝን ሕገ መንግስቱን የማክበርና የማስከበር ኃላፊነቴን ለመወጣት ጭምር ጉዳዩን ወደ ልዩ ልዩ የመገናኛ ብሁሃን አካላትና ከምንም በላይ ደግሞ ወደ ፍርድ አደባባይ/ ፍርድ ቤት በመውሰድ ከላይ ይህ ማመልከቻ በአድራሻ የተላከላችሁ ሁላችሁንም የመንግስት ባለስልጣናትና አካላትን (የመጨረሻውን ፍትሃዊ መልስ ይሰጣሉ ብየ የጠበቀኳቸውን ነገር ግን ፍጹም በማይጠበቅ እጅግ በጣም አሳፋሪና አሳዛኝ በሆነ መልኩ የተጠበቀውን ፍትሃዊ መልስ ባለመስጠት ሕገ-መንግስታዊና ሰብአዊ መብቴ እንዲረገጥ አስተዋጸኦ ያደረጉትን ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ዓሊና በተከበረው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሕግ፣ ፍትሕና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴንም ጨምሮ ማለት ነው) በሕግ ለመፋረድ የምገደድ መሆኔን በጥብቅና በታላቅ ትህትና ለማስታወስ እወዳለሁ፡፡
ከሰላምታ ጋር
አመልካች ዶ/ር ነጋሽ ረዘነ