ጃዋር መሐመድ ተከበብኩ ካለ የሚገደለው አማራ ነው፣ ከአብይ ጋር በስልጣን ከተጣሉ የሚገደለው አማራ ነው

July 8, 2022
ጃዋር መሐመድ ተከበብኩ ካለ የሚገደለው አማራ ነው፣ ከአብይ ጋር በስልጣን ከተጣሉ የሚገደለው አማራ ነው። ኤጀቶ ጥያቄው ካልተመለሰ የሚገደለው አማራ ነው። በዚህች ሀገር የሆነ ነገር ሲፈጠር የሚገደለው አማራ ነው። የሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል። በአማራ ላይ ጀኖሳይድ እየተፈፀመ ነው። ይሄንን በመረዳት ሁላችንም ለመፍትሔው እንነሳ።
መንግስት የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር ማቅረብ ማቅረብ የለበትም። ወልቃይት የአማራና የትግራይ ጉዳይ ብቻም ሳይሆን፣ የምስራቅ አፍሪካ የፀጥታ ጉዳይ ነው።
ኦሀድ ቤንአሚ – የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ
———————————————————-
በአማራ ላይ የሚደረገውን ጀኖሳይድ የሚክዱ ሰዎች፣ ጭፍጨፋው እንዲቀጥል የሚፈልጉ ናቸው። ኢዜማ የሚባለውን ፓርቲ ጨምሮ ከመንግስት ጋር የሚሰሩ በርካታ ፓርቲዎችም ወንጀሉን ጀኖሳይድ አይደለም ብለዋል።
እነዚህ ፓርቲዎች ጀኖሳይዱን የሚክዱት በሀገር እና አለም አቀፍ ደረጃ ጀኖሳይዱ እንዲቆም በተለዬ ሁኔታ እንዳይሰራ፣ በወንጀለኞች ላይ እርምጃ እንዳይወሰድ፣ ሞቱን በመጠባበቅ ያለው አማራም ልዩ ጥበቃ እንዳይደረግለት በማቀድ ነው።
(መስከረም አበራ – ለኢትዮ ንቃት ሚዲያ ከተናገረችው ከተናገረችው የተወሰደ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

እንኳን አገር ቤተሰብ መምራት አትችልም – የአቶ አብይ አህመድ የፓርላማ አሳዛኝና አስቂኝ ጥቅሶች

Next Story

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት

Go toTop