የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከሚሰጥ የአበል ክፍያ ጋር በተያያዘ ያላቸውን ቅሬታ ገለፁ

March 30, 2022
ዛሬ ረቡዕ በሰላማዊ ሰልፍ ገለጹ። ቅሬታ አቅራቢዎቹ የሆስፒታሉ ሰራተኞች፤ ለሁለት ዓመታት ያህል የኮሮና ቫይረስን በመከላከል እና በመቆጣጠር ረገድ ላበረከቱት አስተዋጽኦ በ2012 ዓ.ም ሊከፈላቸው ከሚገባው ክፍያ 34 በመቶ ያህሉ እንዳልተከፈላቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከፊት ለተሰለፉ የጤና ዘርፍ ሰራተኞች የተጨማሪ አበል ክፍያ እንዲደረግላቸው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሁለት ዓመት ገደማ በፊት በመመሪያ ወስኖ ነበር። ግንቦት 14፤ 2012 የጸደቀው መመሪያ በሁሉም የፌደራል ጤና ተቋማት እና የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ተግባራዊ ይሆናል መባሉ ይታወሳል።
የጥቁር አንበሳ ሰራተኞች ከዚህ ክፍያ በተጨማሪ የሶስት ወር የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተፈጸመልንም ሲሉ ያማራርሉ። በሆስፒታሉ ያለው የህክምና ቁሳቁሶች እጥረትም በተመሳሳይ ለሆስፒታሉ ሰራተኞች የቅሬታ ምንጭ መሆኑንም ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። ሰራተኞቹ ዛሬ ረፋዱን ከሆስፒታሉ ቅጽር ግቢ በመውጣት ቅሬታቸውን ለተወሰኑ ደቂቃዎች ማሰማት ቢችሉም በጸጥታ ኃይሎች ወደ ግቢ እንዲመለሱ ተደርገዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የራያ የወሰንና የማንነት ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሠረት እንደሚመለስ የፌዴሬሽን ም/ቤት ገለጸ

Next Story

በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት ቁጥራቸው በወል ያልታወቀ ሰዎች መገደላቸው ተነገረ

Go toTop