ሕወሓት ላይ እጁን እየጠቆመ የሕወሓትን ፖሊሲ የሚያስፈጽመው ደመቀ መኮንን እና ቡድኑ ለስልጣን ሽኩቻ

February 16, 2022

 ለፖለቲካ ሴራ እንጂ ለአማራ ህዝብ ዋጋ አይሰጥም። ደመቀ መኮንን እና ቡድኑ በስልጣን ለመቆየት አማራውን የጦስ ዶሮ እያደረጉት ነው።

በኦሮሚያ ክልል በተለይ በወለጋ በሸዋ የሚገደሉ አማሮች ትኩረት እንዳያገኙ ከኦህዴድ ብልጽግና ይልቅ በደመቀ መኮንን የሚመራው የብአዴን ብልጽግና ከፍተኛ ጥረት በማድረግ የአማራውን ድምጽ ለማፈን ይሯሯጣል። በወለጋ በከፍተኛ ሰቆቃ ውስጥ ያሉ፣ በኦነግ ሸኔ ታፍነው የተወሰዱ፣ በከበባ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ማዳን በየካምፑ ተፈናቅለው ያሉትን መርዳትና ዜጎች ለነገ ዋስትና እንዲያገኙ መስራት ሲገባ ሆን ብሎ እያስጠቃ ፣……… ሆን ተብሎ በአማራው ጭፍጨፋ ላይ የደመቀ መኮንን ቡድን በእጅ አዙር አማራን እያጠቃ ነው። በለውጡ ውስጥ ያልሰራውን ታሪክ እንደሰራ አድርጎ የሚያወራውና የሚያስወራው ደመቀ መኮንን ስሙን ለመገንባት በርካታ ገንዘብ እያፈሰሰ ነው።

ገዱ አንዳርጋቸውንና ቡድኑን ከስልጣን ለማባረር ደፋ ቀና የሚለው ቡድኑ በኦሮሚያ ክልል ለሚጨፈጨፉና ለሚፈናቀሉ አማሮች መብት ደፋ ቀና ቢል ኖሮ ስንት ንፁሃን ዜጎችን ባዳነ ነበር። የደመቀ መኮንን ቡድን ከሕወሓት ዘመን ጀምሮ በተላላኪነት ማገልገሉ ካለተላላኪነት መኖር እንደማይቻል አምኖ ተቀምጦ አማራን በማስጨፍጨፍ የግል ምቾቱን እየጠበቀ ነው። የሃገር ገንዘብ ዘርፎ ለመሸሽ ሲያሟሙቅ የነበረው የደመቀ መኮንን ቡድን ሕወሓት ላይ እጁን እየጠቆመ የሕወሓትን ፖሊሲ እያስፈጸመ ይገኛል። ይህ ቡድን ለአማራው ምንም የማይጠቅም የዜጎችን መብት ለማስከበርም ምንም የማይፈይድ ወራዳ ቡድን ነው። ይህ ቡድን በመላው አማራ ክልል የኦሕዴድ ብልፅግና ደህንነቶች እንዲሰማሩ በመፍቀድ እንዲሁም የመሳሪያ ማስፈታት ፕሮግራሞችን በመምራትና አርሶ አደሩን መቆሚያ መቀመጫ በማሳጣት ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ነው።

አቶ ፀጋ አራጌ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳሉት አቤት ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ዛሬም ፍትህ እየጠየቅኩ ነው። ህግ ይከበር። ለአማራ ብልፅግና ግን ዛሬም ሌላ አንድ የህዝብ ጥያቄ አለኝ። በተለመደው ፍጥነቱ ለጥያቄዬ መልስ ይስጠኝ። የአንድ ኩንታል በወቅቱ የገበያ ዋጋ 5 ሺህ 500 ብር የሸጥከውን ——- ኩንታል ሰሊጥ ያለ ወለድ ተበደርከው? ወይንስ ለማን አከፋፈልከው? ገንዘቡ ከማንና የት እንዳለ ዛሬውኑ መልስ ለህዝቡ እንድትሠጥ እጠይቃለሁ። ከዚህ ውጭ ውርድ ከራሴ። ብለው ብአዴን የሰሊጥ ሌባ መሆኑን አጋልጠዋል።

የኦሕዴድ ብልጽግና ውሸትና የመንግስት ሚዲያዎች የሃሰት ዘገባ ተጋለጠ ! አብዛኛው የመንግስት ሚዲያዎች ዘገባዎች በውሸት የተሞሉ መሆኑ ይህ ሪፖርት አንደኛው ማሳያ ነው።

የከረዩን አባገዳና ሌሎች የገዳው አባላትን በጥይት ደብድበው የገደሉት ፖሊሶች ናቸው። የሟቾችን አስከሬን ለማንሳት ግድያው ወደ ተፈጸመበት ቦታ የሄዱ ሰዎች በቦታው በነበሩ ፖሊሶች እንዳያነሱ በመከልከላቸው ፤ አስከሬኖቹ ለበርካታ ሰዓታት ሳይነሱ መቆየታቸውንና የፈነዱና በከፊል በዱር እንስሳ የተበሉ እንደነበሩ አስከሬኖቹን ያነሱና የቀበሩ ሰዎች ገልጸዋል።
11 የፖሊስ አባላት ተገለውብኛል በሚል የበቀል መነሳሳት የኦሮሚያ ክልል በሰጠው ትዕዛዝ ህዳር 22 ቀን 2014 በግምት ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጥቃቱን ያደረሱ ተጠርጣሪዎችን ለመፈለግ በፈንታሌ ወረዳ ጡጢቲ ቀበሌ ልዩ ስሙ ዴዲቲ ካራ ከሚባል የከረዩ ሚችሌ አባገዳዎችና የጅላ አባላት የመኖሪያ ሰፈር የደረሱ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች 39 የጅላ አባላትን በቁጥጥር ስር አውለዋል። በእነዚህ ፀጥታ አባላት ቁጥጥር ስር ከዋሉ የከረዩ የሚችሌ ገዳ አባላት መካከል 16 ሰዎች ወደ ጨቢ አኖሌ ጫካ ተወስደው14ቱ ሰዎች በጥይት ተመተው ተገድለዋል። አስከሬኖቹ ከጀርባ በኩል ወገባቸውና ጭንቅላታቸው ላይ በጥይት ተመተው መገደላቸውን የሚያሳዩ ምልክቶች ነበሩባቸው።
ከዚህ በላይ መንግስታዊ ሽብር ከየት ሊመጣ ይችላል። መንግስት በወይብላ ማርያም በወለጋና በሌሎች አከባቢዎች ከንጹሃን ግድያ ጋር ስሙ ይነሳል። ይህንን ሊቀርፍ የሚችል ጠንካራ መንግስትና የመንግስት መዋቅር አለመኖር ከፍተኛ ጋሬጣ ፈጥሯል። – https://ehrc.org/…/%e1%89%a0%e1%8a%a8%e1%88%a8%e1%8b…/

ምንሊክ ሳልሳዊ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ካሁን በፊት የአማራ ክልል የሰማዕታት ሀውልት በሚል ይጠራ የነበረው “የአማራ ህዝብ ዝክረ ታሪክ ማዕከል” በሚል ተቀየረ

Next Story

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የፓርላማው ደራማ! – ሰርፀ ደስታ

Go toTop