በቄለም ወለጋ ዞን የጊዳሚ ወረዳ በአሸባሪው ሸኔ 87 ንጹሐን በጅምላ በአንድ ቦታ ተገድለው ተገኝተዋል ሲል የዞኑ አስተዳደር ገለጸ

February 7, 2022
መንግሥት በወሰደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን በቄለም ወለጋ ዞን የጊዳሚ ወረዳ ከአሸባሪው ሸኔ ነፃ መውጣቱን በኦሮሚያ ክልል የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳደር አስታወቀ። የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳደር ተወካይና የዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብሣ በሻ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በጊዳሚ ወረዳ አሸባሪው ሸኔ ዘግናኝ ግድያዎችንና የንብረት ውድመት ፈጽሟል።
በወረዳው በተለያዩ ቦታዎች 81 ሰዎችን እንዲሁም በጅምላ ተገድለው አስከሬናቸው አንድ ቦታ የተገኙ 87 ሰዎችን በድምሩ168 ንጹሐን መገደላቸውን ገልጸዋል።
አሸባሪው ሸኔ በወረዳው በቆየበት ጊዜ 30 የመንግሥት ተቋማትን ንብረቶችን ማውደሙንና ዝርፊያ መፈጸሙን አስታውቀዋል።
አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች፣ ተሽከርካሪዎች ፣ኮምፒውተሮችና ሰነዶች ዝርፊያና ውድመት ደርሶባቸዋል።
የወረዳው አስተዳደር ጽህፈት ቤት፣ ከተማ ማዘጋጃ ቤትና ፖሊስ ጣቢያንም ማቃጠሉን ገልጸዋል።
የሽብር ቡድኑ በትምህርት ዘርፉና በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። በወረዳው የሚገኙ 45 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ አራት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና በስድስት ጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች…
(ኢ ፕ ድ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ለሴረኞች እየመሸ ይመስለኛል በኢትዮጵያ እየሆነ ያለው  ሁሉ ይገለጥ ዘንድ ነው – ሰርፀ ደስታ

Next Story

በዶ/ር ቴድሮስ ወገናዊ መሆን እና አለመሆን ዙሪያ የተነሳ ንግግር

Go toTop