የዐቢይ አህመድ መንግስት ከትግራይ አሽባሪ ኃይሎች ጋር እንደሚደራደር መናገራቸው ተረጋገጠ

January 26, 2022
 አንድ የዳያስፖራ ቡድን ሊቀ መንበር፣ የቡድኑ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ባካሄዱት የግል ውይይት ከትግራይ ኃይሎች ጋር ተኩስ አቁምን የተመለከተ ድርድር ይካሄዳል ሲሉ ዐቢይ እንደነገሯቸው ለአሶስየትድ ፕሬስ ገልጸዋል። የቡድኑ አባላት ከዐቢይ ጋራ ቅዳሜ ለ5 ሰዓታት መነጋገራቸውን የገለጹት የአሜሪካን ኢትዮጵያውያን ህዝባዊ ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀመንበር መስፍን ተገኑ ፣ዐቢይ የሀገሪቱን ጥቅም የሚያስቀድም ምክንያታዊ ድርድር ይካሄዳል ማለታቸውን ጠቅሰዋል። ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያን የጎበኙት የአሜሪካን ልዩ ልዑክ ስለሂደቱ ሃሳብ ሳይኖራቸው እንደማይቀርም ገልጸዋል።
ሁለቱ ወገኖች እንዲደራደሩ ዓለም አቀፍ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም ዐቢይ ግን ድርድር እንደሚካሄድ በይፋ ተናግረው አያውቁም። ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥት ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)ን አሸባሪ ሲል መፈረጁ የኢትዮጵያን መንግስትና ህወሓትን ወደ ድርድር ማምጣትን ፈታኝ አድርጎት ቆይቷል።የህወሓት ኃይሎች ወደ ትግራይ ካፈገፈጉ በኋላ መንግስት ትግራይ ላለመግባት መወሰኑ አቶ መስፍን ፣ የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ፍላጎት የሚጻረር ነበር ሲሉ ተናግረዋል።በዚህ ምክንያት ኮሚቴያቸው በጉዳዩ ላይ ከመንግስት ጋር ለመነጋገር ጠይቆ የዐቢይ ምክትል ወይም የጽህፈት ቤታቸው ሃላፊ ያነጋግሩናል ብለው ሲጠብቁ ዐቢያ ራሳቸው መጥተው እንዳነጋገሯቸው ተናግረዋል።
በዚሁ ወቅትም ዐቢይ «ወደ ትግራይ ክልል አለመግባት የትግራይ ህዝብ ለተዋጊዎቹ ስለሚሰጠው ድጋፍ ቆም ብሎ እንዲያስብ የሚያስገድድ እንደሚሆንና ለመንግሥትም ጊዜ እንደሚሰጥ» ነግረውናል ብለዋል።አሶስየትድ ፕሬስ በጉዳዩ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ ብሌነ ስዩምም ሆነ ከህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ አስተያየት ለማግኘት ቢሞክርም እንዳልተሳካላት ዘግቧል።
DW

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የዓለም ጤና ድርጅትን መርህ በመጣስ በሚንቀሳቀሱት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ላይ ክስ ቀረበ

Next Story

የሚኒስትሮች ምክር ቤት 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ውሳኔ

Go toTop