የብርሃኑ ነጋ እህት እስካለ ነጋ (ነፍስ ይማር) እና መለስ ዜናዊ የአንድ ዘመን እኩያ ተማሪዋች ነበሩ። ሁለቱም በ1965 ዓመት ምህረት ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ጎበዝ ተማሪዋች ነበሩ።
አስካለ ነጋ ከመድሃኒአለም መለስ ዜናዊ ከዊንጌት በብቸኝነት ከመላ የሀገሪቱ ትምህርት ቤት ተማሪዋች ከፍተኛ ውጤት አምጥተው ሁለቱም ዮኒቨርስቲ በመግባታቸው ከንጉሱ በወር በወር የመቶ ብር ተከፋይም ነበሩ።
አስካለ ነጋ የኢህአፓ ሴል ሆና ስትንቀሳቀስ በመንግስት ሃይሎች አይን ገብታ መሐል አራት ኪሎ ከዩኒቨርስቲው በር ላይ ራሳዋን የጉሊት ሴት አስመስላ ስትንቀሳቀስ ተቱኩሷባታ ህይወቷ አልፍል።
መለስ ዜናዊ ደሞ ትምህርቱን አቋርጦ፤ ጭካ ገብቶ፤ ዘመን ጠብቆ፤ ድል ቀንቶት፤ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆኖ በስተመጨረሻ ባዮሎጂ ስራውን ሲጨርስ አልፎል።
ብርሃኑ ነጋ የእህቱን የአስካለ ነጋ የተማሪ ቤት ጓደኛ፤ የመለስ ዜናዊን እውቀት እና ጉብዝና በሚገባ ያውቅ ነበርና በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ መክሮት ያውቃል።
“አሁን አንተ የታላቂቷ ሀገር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ነህ። በአንተ የመሪነት ዘመን ኢትዮጵያ ወደ ዲሞክራሲ ወደ እኩልነት ወደ ፍትህ ወደ ስልጣኔ ተለወጠች የሚል ታሪክ ከመስራት ወደ ኃላ እንዳትል። ከዚህ ውጭ ምንም የምትፈልገው ነገር መኖር የለበትም። ለአንተ ካለህ ብቃት አንፃር ገንዘብ፣ ስልጣን፣ እውቅና ምንም ናቸው።” ሲል ብርሃኑ ነጋ መለስ ዜናዊን መክሮታል።
መለስ ዜናዊ ግን የብርሃኑ ነጋን ምክር የሩብ ሩብ ለመፈፀም አንዳች ፍላጎት ሳይኖረው ዘመኑን ጨረሷል። መለስ ዜናዊ ‘የጉራጌ ነፃ አውጪ’ እያለ የሚቀልድበትን ብርሃኑ ነጋን ሰምቶት ቢሆን ኖሮ የሀገራችን ታሪክ ዛሬ ላይ ሌላ በሆነ ነበረ።
ብርሃኑ ነጋ ምክሩን አልሰማ ብሎት ሀገርን ከድጥ ወደማጡ ሲያወረዳት ሲያይ በመለስ ዜናዊ ላይ ነፍጥ ለማንሳት አላቅማማም።
ዛሬ ብርሃኑ ነጋ በመለስ ዜናዊ እና በድርጅቱ መቃብር ላይ የኢትዮጵያ ካስማ በሆኑት በአፋሮች መንደር አፋሮችን መስሎ በክብር ቆሞል።
ብዙዋች ብርሃኑ ነጋን ለምን አምርረው እንደሚጠሉት ይገርመኛል። የቆሎ ተማሪ ‘ውሻ ለምን ይጮኽብሃል’ ሲባል ‘ቁራሹን ስለምወስድበት’ ብሎ ይመልሳል። እናም የብርሃኑ ነጋ ነገር የግር እሳት የሚሆንባቸው ሰዋች የመለስ ዜናዊ ነገር እየሆነባቸው ይሆንን??? አላቅም።
ምንም ቢሆን ግን ሰውዬው የት መገኘት እንዳለበት ጠንቅቆ የሚያቅ ፕሮፌሰር ነው።