አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ህዳር 24 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መንጌ ወረዳ፣ ጎልሞሶ ቀበሌ ላይ የቤህነን ታጣቂ ቡድን መሪ የሆነው ህድር መሐመድ አሊ በቁጥጥር ሥር ውሏል።
የታጣቂ ቡድኑ መሪ በቁጥጥር ሥር በዋለበት ወቅትም ክላሽ 1፣ ካርታ 2፣ የክላሽ ጥይት 60፣ የጭስ ቦምብ 5፣ ሞቶሮላ ሬዲዮ መገናኛ 1 እና የሱዳን ወታደራዊ ልብስ አብሮ መያዙን የቤጉ ክልላዊ መንግስት መ/ኮ/ጉ ጽ/ቤት ዘግቧል።