የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አባላት ወደ ግምባር ለመዝመት መዘጋጀታቸውን ገለጹ

November 24, 2021
የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አባላት ወደ ግምባር ለመዝመት መዘጋጀታቸውን ገለጹ፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቀብሎ አገሪቱን ከህወሓት ወራሪ ሀይል ማዳን እንደለበትም ገልጸዋል፡፡
የትግራት ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ዶክተር አረጋዊ በርሄ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣውን ወረራ ከሌሎች የአፍሪካ ወንድሞቻችን ጋር በመሆን መመከት ይኖብናል ብለዋል።
በርካታ ግለሰቦችና ሚዲያዎች የሐሰት መረጃ በማሰራጨት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ትልቅ ውዥንብር እየፈጠሩ ነው።
ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ በራሷ ጥረትና እውቀት ማደግ እንደምትችል ማሳየቷ ባይወደድላትም የአድዋን ድልና የአባይ ግድብ ማሳያ ነው ያሉት ዶክተር አረጋዊ የተቃጣብንን ጦርነት በመመከት ነጻነታችንን እናረጋግጣለን።
ለአፍሪካ ነጻነት ሲሉ አፍሪካውያውን ከኢትዮጵያ ጐን ሊቆሙ ይገባል። ነጻነት ለሚሻ ህዝብ ኢትዮጵያ ምሳሌ ነችም ብለዋል። በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገው ጦርነት በሁሉም የአፍሪካ አገራት ላይ እንደተረገ በመቁጠር ሁሉም አፍሪካዊ ኢትዮጵያን ማገዝ እንዳላበት ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው የህወሓት ቡድንን ለመደምሰስ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ተነስቷል፣ በብር ስለደነዘዙ ይህ አልታያቸውም። እንዲሁም ከግራና ከቀኝ ያለው የአማራና የአፋር ክልል ህዝብ የሚገባቸውን ዋጋ እየሰጣቸው ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በሞገስ ተስፋ
(ኢ ፕ ድ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

እምቢ በይ ኢትዮጵያ! – በላይነህ አባተ

Next Story

የጋሸናና የሸዋሮቢት ሁኔታ – ግርማ ካሳ

Go toTop