የምዕራብ ጎንደር ዞን የፍኖ እና ሚሊሻ አባለት በገንዳውሃ ከተማ አስተዳደር ወደ ግንባር ሽኝት ተደረገላቸው

November 25, 2021
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ህዳር 16 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ
በምዕራብ ጎንደር ዞን የፋኖ እና የሚሊሻ አባላት በገንዳውሃ ከተማ አስተዳደር ወደ ግንባር ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
ያነጋገርናቸው የሚሊሻ እና ፋኖ አባላት እንደተናገሩት ወራሪው የጁንታ ቡድን በሃገርችን በተለይም በክልላችን ያሉ ሰላማዊ ሰዎችን በመግደል ፣ነብሰ ጥሩ፣ ህፃናት ፣መነኩሴዎችን በመድፈር ፣መሠረት ልማቶችን በማውደም ከፍተኛ የሆነ ኢሰባዊ ተግባር ሲፈፅም መቆየቱን ገልፀዋል።
በመሆኑም እኛ እያለን አገራችን መፍረስ የለባትም፤ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዘምተዋል እኛም ወደ ግንባር በመዝመት ሃገራችንና ህዝባች ከስቃይ ለመታደግ ወደ ግንባር እየተሸኘን እንገኛለን ብለዋል።
ዘማቾች አያይዘዉ እንደገለፁት አሁን የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም አካላት በጉልበቱ ፣በገንዘቡና በእውቀቱ የተቻለውን ሁሉ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባው መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል ሲል የገንዳውሃ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

እውን ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ በኢትዮጵያ ላይ እያሴሩ ነው? – ሰርፀ ደስታ

Next Story

ምሽት 12፡00 ዜና ሙዳይ ባሕር ዳር፡ ሕዳር 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ)

Go toTop