ቤተ ክህነት ውስጥ የተገኘው ጥይት በሕጋዊ ኹኔታ ሲተላለፍ የቆየ መኾኑን የሚያሳየው መረጃ ይፋ ኾነ፡፡ ቤተ ክህነቷን በሞላ አሸባሪ ለማለት ተፈልጎ ካልኾነ በቀር የምትመለከቱት ሰነድ እነዚህን ጥይቶች የአሁኑ የግምጃ ቤት ኃላፊ ጌትነት ታፈሰ ከቀድሞው ኃላፊ ከመሪጌታ ጥበቡ የተረከቡበት ማስረጃ ነው፡፡
የተረከቡበት ቀን ጳጉሜን ፳፻፲፫ ዓ.ም.
ተረካቢ፡- ጌትነት ታፈሰ
አስረካቢ፡- መሪጌታ ጥበቡ ተፈራ
አረካካቢ፡- ፩. መ/ር ኃ/ገብርኤል ተሰማ
፪. አ/ር ዮሐንስ ስለሺ
፫. አቶ ኢዮብ ድባቤ
መሪጌታ ጥበቡ ወደ ፲፬ ዓመታት በቦታው ላይ ነበሩ፡፡ እነዚህም ጥይቶች አብረዋቸው ነበሩ፡፡ ጊዜአቸው ሲደርስም ዘአወፈየኒ አወፈይኩከ ብለው ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡ ዛሬ የታሠሩት ወንድማችን አደራው እንዲህ ነው የደረሳቸው፡፡
በዚህ መንገድ መዝገብ ነክሶ በቬርባል (ቤተ ክህነታዊ አባባል ነው) ርክክብ የተደረገበትን ሥርዓት ያለው ሒደት አባጣ ጎባጣ ትርጉም በመስጠት ታሪክ አታበላሹ፡፡ የፈለጋችሁት ምን እንደኾነ ግልጽ ነው፡፡ ተቋሟን ወንጀለኛ ለማድረግ የታቀደ ሤራ ከቆየው የጠላትነት ፍረጃ ይመነጫል፡፡
እሥረኛውን ፍቱ!!!
ሰው የላትም መሰል ቤተ ክህነቷም አንድም ፈርታ አንድም አድልታ አቋቋሟ ተዛምሟል፡፡
–
አባይነህ ካሴ