የሕወሓት ቅጥረኛው ማርቲን ፕላውት የሀሰት ዜናን ስለመፍጠር ሲያሰለጥን የሚያሳይ ምስል ወጣ

November 16, 2021
ኢትዮጵያ ላይ የውጭ ጫናን ለማበርታት የአሸባሪው ሕወሓት አፈቀላጤ ሆኖ እየሰራ የሚገኘው ማርቲን ፕላውት የሃሰት ዜና እንዴት መፍጠር እንደሚቻል ሲያሰለጥን በድብቅ የተቀረፀው ተንቀሳቃሽ ምስል ወጣ።
የአፍሪካ ቀንድን ፖለቲካ ለዓመታት ያጠናውና የ”አንደርስታንዲንግ ኤርትራ” መጽሐፍ ደራሲው አሁን ላይ የለየለት የሽብር ቡድኑ ሕወሓት የውጭ አገር አፈቀላጤ ሆኖ እየሰራ ነው።
በዚህም በየደቂቃዎች ልዩነት በኢትዮጵያ ላይ የሀሰት ዜና በማሰራጨት የተጠመደው ማርቲን ፕላውት እንዴት የሀሰት ዜና እንደሚሰራ አገር ለማፍረስ አጋርነት ለፈጠሩት የጥፋት መልዕክተኞች ሥልጠና ሲሰጥ የሚየሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ወጥቷል፡፡
“ለቪኦኤና ለቢቢሲ ትግርኛ ለዜና የሚሆን መረጃ ልንሰጣቸው እንችላለን በእርግጥ መገናኛ ብዙኃኑ የዜና ረሃብ ያለባቸው በመሆናቸው ያለንበትን እውነታ ከግምት ውስጥ ለማስገባት ማሰብ አይጠበቅብንም” ሲል ተደምጧል፡፡
“ጋዜጠኞች አንድ ህዋስ ያላቸው ቀላል ፍጡራን ናቸው፤ ነገሮችን ይፈልጋሉ፤ ጎግልን ይፈትሻሉ ነገር ግን አያጤኑትም ያገኙትን ያወጣሉ” ሲል እነሱ ስለሚዘውሯቸውና በጋዜጠኝነት ካባ መገናኛ ብዙኃን ውስጥ ስለገቡ አካላት ይገልፃል።
“የሀሰት ዜናውን መስራት አስፈላጊ ነው፤ መስራቱ ያን ያክል ከባድ ላይሆን ይችላል ብሏል” በድብቅ ተቀርፆ በተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል፡፡
ዜናው ሲፈበረክ ስለሚሰራበት አቅጣጫ ማስተዋል እንደሚያስፈልግም ለቅጥረኛ ሰልጣኞቹ ይመክራል፡፡
ኅዳር 7/2014 (ዋልታ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

❝ወቅቱ አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያውያን በጋራ የምናጠፋበት ነው❞ አርቲስት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ

Next Story

ለቸኮለ! ማክሰኞ ኅዳር 7/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

Go toTop