«ሕወሓት ከአዲስ አበባ ሌላ ጉዳይ የለውም» ጌታቸው ረዳ

November 8, 2021

በትግራይ ክልል ላይ የተጣሉ ዕቀባዎች ከተነሱ እና የተቋረጡ አገልግሎቶች ከተመለሱ ሕወሓት የተኩስ አቁም ለማድረግ እና ለመደራደር ፍቃደኛ መሆኑን የግንባሩ ቃል አቃባይ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ ። ቃል አቃባዩ ዛሬ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ «ሕወሓት ከአዲስ አበበ ሌላ ጉዳይ የለውም» በትግራይ ክልል ላይ የተጣሉ ዕቀባዎች ከተነሱ እና  የተቋረጡ አገልግሎቶች ከተመለሱ ሕወሓት የተኩስ አቁም ለማድረግ እና ለመደራደር ፍቃደኛ መሆኑን የግንባሩ  ቃል አቃባይ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ ። ቃል አቃባዩ ዛሬ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ «ሕወሓት ከአዲስ አበባ ሌላ ጉዳይ የለውም» ብለዋል።
በአፍሪቃ ቀንድ የአፍሪቃ ሕብረት ልዩ ልዑክ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ከሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸውን ያነሱት አቶ ጌታቸው ፤ የንግግሩ ይዘት  በሂደት ያለ በመሆኑ ዝርዝር ጉዳዮችን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።
የሕወሃት ቃል አቃባይ ጌታቸው ረዳ ድርጅታቸዉ ይፈፅማቸዋል ስለተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ከሕዝብ ስለሚደርስበት ተቃዉሞ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ይሰጠዋል ስለሚባለዉ ድጋፍ፣ ከሌሎች ስምንት ቡድናት ጋር ስለመሰረተዉ ትብብር እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።
ነጋሽ መሐመድ አነጋግሯቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ልጆቹንም ሀብቱንም በሚገብረው ሕዝብ ስም የድርድሩ ድንበር የት ድረስ ነው?

Next Story

፲፩ኛ ስዓት፡ ዕድል እና ገደል= ገድል + ድል

Go toTop