አ/አ እህል በረንዳ አካባቢ የተነሳው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ

October 30, 2021

በቁጥጥር ስር የዋለው የእህል በረንዳው የእሳት አደጋ
ጥቅምት 20/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መሳለሚያ እህል በረንዳ አካባቢ አማኑኤል ፀጋ አብ ህንፃ ላይ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ።
ከ1 ሰዓት በፊት ዋልታ የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር እና ወደ ሌሎች እንዳይዛመት የእሳትና ድንገተኛ አገልግሎት ባለሙያዎች፣ የፖሊስ አባላት እና የአካባቢው ወጣቶች እየተረባረቡ እንደሚገኙ መዘገቡ ይታወሳል።
በቀጣይም የእሳት አደጋውን መንስኤ፣ በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት እና ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን መረጃ እንደሚሰጡ የከተማዋ ፕሬስ ሰክሪታሪያት አሳውቋል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ

በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መሳለሚያ እህል በረንዳ አካባቢ አማኑኤል ፀጋ አብ ህንፃ ላይ የእሳት አደጋ ተከሰተ።
የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር እና ወደ ሌሎች እንዳይዛመት የእሳትና ድንገተኛ አገልግሎት ባለሙያዎች፣ የፖሊስ አባላት እና የአካባቢው ወጣቶች እየተረባረቡ ይገኛሉ።
የእሳት አደጋውን መንስኤ፣ በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት እና ተያያዥ ጉዳዮች የምርመራ ውጤት አጠናቅሮ አስተዳደሩ ይፋ እንደሚያደርግ የከተማዋ ፕሬስ ሰክሪታሪያት አሳውቋል።
ጥቅምት 20/2014 (ዋልታ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ለቸኮለ! ቅዳሜ ጥቅምት 20/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

Next Story

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ሰጥቷል።

Go toTop