የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአሁኑ ወቅት ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉለት ጥሪ አቀረበ

October 8, 2021
ደሴ፡መስከረም 28/2014 ዓ.ም
ዳግማዊ ተሠራ/አሚኮ

dese1

የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች እና ለህልውና ዘመቻው አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ሃይማኖት አየለ (ዶክተር) ገልጸዋል። ሆስፒታሉ በአሁኑ ወቅት ልዩ እገዛ የሚያስፈልገው በመሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ሥራ አስኪያጇ እንዳሉት የሰሜን ወሎ ሆስፒታሎች በአሸባሪው ትህነግ ወረራ ምክንያት በመዘጋታቸው እና በመውደማቸው ተፈናቅለው በደሴ ከተማ የሚገኙ ዜጎችን ጭምሮ ለአካባቢው ኅብረተሰብ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ብቸኛ የመንግሥት ሆስፒታል በመሆኑ መጨናነቅ ፈጥሯል።
በተለይም በሆስፒታሉ ያለጊዜያቸው የሚወለዱ የጨቅላ ሕጻናት ህክምና በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ እንደሚገኝ ነው የገለጹት። አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 320 እናቶች መውለዳቸውን ለአብነት አንስተዋል። ከዚህ ውስጥ ደግሞ አብዛኛዎቹ አካባቢያቸውን ከለቀቁ እናቶች የተወለዱ ሕጻናት በመሆናቸው ሕጻናቱ በምግብ እጥረት የተጎዱ ናቸው ብለዋል፡፡
እነዚህ ሕጻናት የህክምና ክትትል የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ በሆስፒታሉ ህክምና እየተሰጣቸው ይገኛሉ ነው ያሉት።
ሆስፒታሉ ካለበት የሥራ ጫና አኳያ አገልግሎቱ ቀጣይነት እንዲኖረው መንግሥት ከሚያደርገው ድጋፍ ባለፈ ሌሎች አጋር አካላትም ድጋፍ እንዲያደርጉ ዶክተር ሃይማኖት ጠይቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የኢትዮጵያ አየር መንገድ CNN ያሰራጨዉን ዘገባ እንዲያርም ጠየቀ

humera, amhara, ethiopia
Next Story

በአሸባሪው የትህነግ ቡድን የወደሙ የትምህርት ግብዓቶችን በማሟላት የመማር ማስተማር ሂደቱን ማስጀመሩን የሁመራ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ

Go toTop