ብሄራዊ ጥቅምን በሚነኩ ማናቸውም ጉዳዮች ዙሪያ ከህዝብና ከመንግስት ጎን እንደሚቆም ኦነግ አስታወቀ

August 19, 2021

235949204 4710588915639614 5968924650408157765 n

የአገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚነኩ ማናቸውም ዓይነት ጉዳዮችን በሚመለከት ከህዝብና መንግስት ጎን እንደሚቆም የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አስታውቋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባሳለፍነው ሚያዚያ “ህወሓት” እና “ሸኔ”ን በአሸባሪነት መፈረጁ ይታወሳል።

ሁለቱ አሸባሪ ቡድኖች በቅርቡ ህብረት መፍጠራቸውን ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ መንግስት አሸባሪ ቡድኖቹ ፈጠርን ያሉት ህብረት አዲስ ጉዳይ እንዳልሆነና ቀደም ብለውም ኢትዮጵያን ለማፍረስ በጋራ ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውቋል።

አሸባሪዎቹ ሸኔ እና ህወሓት የፈጠሩት ትብብር የኦሮሞ ህዝብ ለነጻነቱ ያደረገውን ትግል የካደ መሆኑንም ግንባሩ ገልጿል።

የኦነግ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ቃጄላ መርዳሳ አሸባሪ ቡድኖቹ የፈጠሩት ትብብር “የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን አይመለከትም” ያሉ ሲሆን፤ ትብብሩ የአገርን ሕልውና አደጋ ላይ የመጣል ዓላማ እንዳለውም አብራርተዋል።

ሁለቱ አሸባሪ ቡድኖች የሚከተሉት አገር የማፍረስ እንቅስቃሴ “በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት የለውም” ብለዋል።

የአሸባሪ ቡድኖቹ ትብብር አዲስ ጉዳይ እንዳልሆነ ጠቁመው፤ ቀደም ብለውም በጋራ ሲሰሩ መቆየታቸውን አቶ ቃጄላ ገልጸዋል።

አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ባስተዳደረባቸው ጊዜያት ራሱ ብቻ ተጠቃሚ እንደነበር አስታውሰው፤ በዚህም ቡድኑ በህዝብ አመጽ ከስልጣን መወገዱን ተናግረዋል።

ከአሸባሪው የህወሓት ቡድን መሰረታዊ ባህሪያት አኳያ ከሸኔ ጋር የፈጠረውን ትብብር የራሱን ፍላጎት ብቻ ለማሟላት በጊዜያዊነት ሊጠቀምበት እንደሚችልም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ኦነግ የአገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚነኩ ማናቸውም ዓይነት ጉዳዮችን በተመለከተ  ከህዝብና ከመንግስት ጎን እንደሚቆምም አረጋግጠዋል።

“እኛ ተቃዋሚዎች ነን፤ የአገሪቷን ብሔራዊ ጥቅም የሚነካ ነገር ሲኖር ደግሞ አብረን እንቆማለን” ሲሉ ነው አቶ ቃጄላ ያረጋገጡት።

አሸባሪዎቹ ሸኔ እና ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚያደርጉትን የሴራ ትብብር የሚያወግዙ ሰልፎች በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄዱ መሆኑን የኢዜአ ዘገባ አስታውሷል።

EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published.

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ ምልምል የልዩ ኀይል ፖሊሶችን እያስመረቀ ነው
Previous Story

አማራ የተሰጠውን ዕድል እንደማያበላሽ ተስፋ አደርጋለሁ!! – አምባቸው ዓለሙ (ከደሴ)

tefera mamo
Next Story

ጠላትን በአጭር ጊዜ ለማጥፋት በቅንጅት እየተሰራ ነው፡- ብ/ጄ ተፈራ ማሞ

Go toTop