ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ነጭ ነጯን!! ከኮረም እስከ ወልዲያ የተፈፀሙ አሳፋሪ ድርጊቶችን አጋለጠ!!!! | ENDF | Woldiya
የወሎ አማራ ተሸጧል
እኔ በራያ ግምባር ከዋጃ ጀምሮ በጦርነቱ ተሳትፌያለው ። በሁሉም ግምባር ማለት ይቻላል ። በሚዲያ እንደምንሰማው የፋኖም ሆነ የክልል ልዩ ሃይሎች በጦርነቱ አላየሁም ።
የተወሰነ ጦርነት እያካሄዱ ያሉት የአማራ ልዩ ሃይልና በቁጥር ትንሽ የሆኑ የመከላከያ ሰራዊት ናቸው ።
ጠላት ይመጣል ። እኛም ቦታ ይዘን እንጠብቃለን ከመከላከል ወደማጥቃት ስንሄድ አፈግፍጉ የሚል ድምፅ እንሰማለን ። ወደኋላ አፈግፍጉ ።
በጦርነቱ መካከል የወገን ጦር ነው የተባለው ኃይል ከኃላ ወግቶናል ።
በ4 ግምባሮች ተሰልፌያለው ። በሁሉም ቦታ ይህ ነው የሚባል ጦርነት አልተካሄደም ። በቃ አፈግፍጉ በሚባል ሠዓት መከላከያ ሰራዊቱ ትጥቁን ጭምር ለወያኔ ጥሎ ነው የሚያፈገፍገው ።
ከዛም . ከ2 መቶ የማይበልጡ የወያኔ ሚልሻዎች አቋርጠው ሌላ ከተማና ወረዳ ያዝን ብለው የጥይት ድምፅ ሲያሰሙ አስቀድሞ የሚፈረጥጠው አመራሩ ነው ። የአማራ ክልል አመራሮች ከፍተኛ የሆነ ድክመት አለባቸው ። አገር በውሸት አትመራም ።
ለምን እንወሻሻለን ? የወሎ አማራ ተሽጧል ።
ከፍተኛ ለወታደራዊ ስልጠና የተዘጋጁና ያልሰለጠኑም ወጣቶች ህይወታቸውን ለመስጠት ቆራጥ ነበሩ ። ግን ምን ያደርጋል ፡ አስታጥቁን ሲሉ ለናንተ መሳሪያ አንሰጥም ። ችግር ልትፈጥሩብን ትችላላችሁ ነው የተባሉት ።
ክተት ብሎ አውጆ ግምባር ላይ የስንቅና ትጥቅ አቅርቦት ሳይኖር ፡ ክተት ብቻ ምንም ቁም ነገር የለውም ።
የወልድያ ወጣቶች ቆራጦች ናቸው ።መሳሪያ መንግስት አስታጥቋቸው እንዳይመስልህ ። በጥልቆም ፡ በገጀራም በተገኜው ነው እየተዋደቁ ያሉት ።
ዋና ችግሩ የአመራሩና የመከላከያ ነው።
አርቲስት ዱባለ መላክ