አይበልናንዶ – የአብይ አህመድ የፖለቲካ ቁማርና የተሾረበው የእልቂት አሻጥር (ከእውነቱ)

July 13, 2021
abiy
abiy

ጠርጣራው በሚል ስም የሚታወቀው የትህነግ ዘፋኝአይበልናንዶሲል ኤርትራን ለማስጠንቀቅ የዘፈነው ዘፈን የአማርኛ ትርጉሙብለን ነበርማለት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከሁለቱም አገሮች የህዝብ እልቂቱና ሁሉም መሆን ያልነበረባቸው ክፉ ነገሮች ሁሉ ሆነው ካለፉ በኋላ ጉዳዩን አሁን ላይ ቆመን መሬት ላይ ያለበትንና ይግባኝ የሌለበትን የክስና ፍርድ ውሳኔ ስናጤነው ተዳፍኖ ይብሰል የሚያሰኝ ነው፡፡

እዚህ ላይ አይበልናንዶን ያነሳሁት ስለባድመ ጉዳይ ለመዘገብ ሳይሆን አብይ አህመድ ታላቋን ኢትዮጵያ ብዙወቻችን ብለን እንደነበረው ባህር ውስጥ እያሰመጣት እንደሆነ ለማሳዬት ነው፡፡ አብይ ልብ ቢኖረው ኖሮ፣ ኢትዮጵያን ቢወድ ኖሮ፣ ከኦሮሙማ ተላቅቆ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን በእኩልነትና በሀቅ የቆመ ቢሆን ኖሮ አምባገነንም ቢሆን ከኢሳያስ አፈወርቂ ብዙ መማር ይችል ነበር፡፡ ኢሳያስ አፈወርቂ አምባገነን ከመሆኑ ውጭና አገሪቱን እስካሁን ከድህነት አሮንቃ ማውጣት ካለመቻሉ በስተቀር (ይህም በትህነግ በኩል በአሜሪካ መሪነት የምአራባዊያን የተጽአኖ እጅ ስላረፈበት ነው) ኤርትራ የምትባል አገር መስርቶ የመሰረታትንም አገር ነጻነት ጠብቆ፣ በአገሩ ጉዳይ ለማንም የውጭ ሀይል ቅንጣት ሳይንበረከክና ከጎረቤትም በከሀዲወቹና በመዥገሮቹ ትህነጎችም ጉዞው ሳይሰናከል ኤርትራ እራሷን አስከብራና የህዝቧን ደህንነት አረጋግጣ በነጻነቷ አሸብርቃ እዚህ እንዲትደርስ አብቅቷታል፡፡አብይ አህመድ ከኢሳያስ አፈወርቄ መጥፎ መጥፎውን ትቶ ጥሩ ጥሩውን በመውሰድ ትምህርትና ልምድ ቢቀስም ኖሮ ስልጣን ላይ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ የህዝቡን ደህንነትና የአገሩን አንዲነት ጠብቆ መጓዝ ይችል ነበር፡፡ ዳሩ ግን የኦሮሙማው ያልተነቃበት ቁጥር አንድ ቀንደኛ አብይ አህመድ እንደ አገር ለኢትዮጵያና እንደ ህዝብም ለኢትዮጵያዊያን የቆመ ስላልሆነ የተጠረጠረው፣ የተፈራውና እኛምብለን ነበርያልነው ሆነ፡፤ ቢሆን ኖሮ የሚለው ሁሉ ሳይሆን ቀርቶ ይህች ታላቅ አገር በዚህ ትንሽ ሰው እጅ ወድቃ ለዚህ በቃች፡፡

አማራን በሚመለከት የአብይ አህመድ የፖለቲካ ቁማር ምን ያህል የረቀቀ እንደሆነ አንድ ትኩስ ማሳያን ብቻ እንጥቀስ፡፡ አንድ ወቅት አክራሪ ጸረ አማራ አሰላለፍ የነበረው አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ አሁን ላይ ተነስቶ ራያ፣ ወልቃይት፣ ጠገዴ የአማራ ናቸው ብሎ አብይ እንዲናገር ሲያደርገው በሌላ በኩል ደግሞ / ደረጀ ደገፋ ቱሉ አማራ ከነዚህ ቦታወች በሙሉ መውጣት አለበት ብሎ እንድናገር አድርጎታል፡፤ ሁለቱም ሰዎች ቁልፍ የኦሮሙማ ሰወች ሲሆኑ በአብይ አህመድ ሻጥረኛ ፖለቲካ ፍጹም ተቃራኒ ሀሳብን እንድናገሩ ተደርጓል፡፡ ይህ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው፡፤ አብይ አህመድ ማለት ይህ ነው፡፡

አብይ ስልጣን እንደያዘና ህዝቡም ያንን ያህል ብሎ እንደደገፈው ሁሉ ወያኔ የጻፈውን ህገ መንግስት ተብየ ከማገድ ጀምሮ አያሌ መስተካከል ይገባቸው የነበሩ ብዙ ነገሮችን በትኩሱ አስተካክሎ ቢሆን ኖሮ ያሁኑ ምስቅልቅል ፈጽሞ አይከሰትም ነበር፡፤እዚህ ላይ በቅርብ የተካሄደውን የሱዳኑን ፈጣንና ስር ነቀል የመንግስት ውጤታማ እርምጃወች ያጤኗል፡፡ ኢትዮጵያችንን አሁን ከሚታየው ምስቅልቅል የሚመጣው ገና ብዙ ያስፈራታል፡፤ ትህነግ የሰሜኑን ጦር በማረድ ለጀመረው አሳዛኝ ጦርነት ገፈት ቀማሹ የአማራ ልዩ ሀይል ግስጋሴውን በወሳኝነት ከገታው በኋላ በውጊያው የኢትዮጵያ ጦር ድል ቢያደርግም ትንሽ ቆይቶ አብይ አህመድ በጸረ ኢትዮጵያ የተቀነባበረ የውጭ ሀይሎች ታዝዞ ትግራይን ለቅቆ ወጣ፡፤ ሁሉ መስዋእትነት ዉሀ በላው፡፤

ይታያችሁ፡፡ትህነግ ክህገ መንግስት በፊት አማራውን በማፈናቀል፣ በመግደልና ዘር በማጽዳት በጉልበቱ የወሰዳቸውን የአማራ የወልቃይት ራያ ጠገዴና ጠለምት መሬቶች የአማራ ፋኖ፣ ልዩ ሀይልና ሚሊሽያ በደሙ ካስመለሳቸው በኋላ ሁሉም ባለበት ቆሞ የፖለቲካ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ የትህነግ ሀይል መልሶ ቦታወቹን እንዲይዛቸው እንዲደረግ ከአሜሪካ በተሰጠው ቀጭን ትእዛዝ መሰረት በአሁኑ ሰአት የአማራ ሀይል ቦታወቹን ለቅቆ እንዲወጣ እያዘዘ ቦታወቹን የትህነግ ሀይል እንዲይዛቸው እያስደረገ ነው፡፡ የአማራ ብልጽግና ተብየው ድንዝዙና ሆድ አደሩ ብአዴንም እንደለመደው ዛሬም በበታችነትና በታዛዝነት የአማራን ታላቅ ህዝብ አዋርዶ በተረኛው ኦሮሙማ ድጋሜ ህዝቡን በማስመታቱ ታሪክ ለፍርድ ያቀርበዋል፡፤

ሰውየው ለምንና ለማን ብሎ ይህንን ከባድ የአገር ክህደት የፈጸመበትን ሁለት መሰረታዊ ምክንያቶችን እንጥቀስ፡፡ አንደኛው ምክንያት ግለሰቡ ራሱን ፣ሚስቱንና ልጆቹን ከማንም በላይ ስለሚያስበልጥ በአሜሪካ የተጣለበት የማስፈራሪያ ማእቀብ ተነስቶለት ልጆቹና ሚስቱ በአሜሪካ ወደነበሩበት ደንቨር ኮሎራዶ እንዲገቡ ለማስቻልና እርሱም ማእቀቡ እንዲነሳለት ለማደረግ ከአሜሪካኖች ጋር በውስጥ ስለተደራደረ ይህንኑ ተፈጻሚ ለማድረግ ነው፡፡ ይህንኑ እውን ለማድረግ አሜሪካኖቹ አድርግ ያሉትን ሁሉ ገና ያደርጋል፡፡ ሁለተኛው ምክንያት የተዘፈቀበት ኦሮሙማ ነው፡፡ ሰሜኑ እንዲህ እየታመሰ ኦሮሚያን መስላና ኦሮምያን ሆና በአዲስ መልክ እንድትፈጠር ኦሮሙማወች የሚጥሩላት አዲሷ ኢትዮጵያ አትፈጠር፡፡ የሚያልሟት ኢምፓየርም፣ የኦሮሙማው ስብስብና ቁንጮ መሪውም አንዲትም ቀን በሰላም አይኖሩም፡፡ለጊዜው እርሱ ባደለበው ልዩ የሪፐብሊካን ጋርድ ፣ተስፋፊው የኦሮምያ ክልልም 21 ዙር ባሰለጠነው፣ በመቶ ሽህወች በሚቆጠረውና እስከ አፍንጫው በታጠቀው የኦሮሞ ልዩ ሀይል እድሜያቸው ሊራዝም ይችል ይሆናል፡፡ ቤተሰቤን አሜሪካ ሰዲጄ በሰላም ይኖሩልኛል የሚለው ህልሙ ግን ለአጭር ጊዜም ቢሆን አይሰራም፡፡በፈለገ ሀይል ቢያስጠብቃቸውም፡፤ አይሰራም!!

ስለዚህ መላው ኢትዮጵያዊና በተለይም መላው አማራ ሆይ፦ ይህ የኦሮሙማ ቁንጮና የውጭ ገዥወች ታዛዥ ሰው መሪህ አይደለም፡፤ አንድ በአንድ ሳያስጨርስህ በፊት ተነሳ፡፡ስርአቱን መንግለህ ጣል፡፡ 27 ዓመታት የምታውቃቸውንና ርህራሄ የለሾቹ የትህነግ ጅቦችንም አስቁማቸው፡፤የአብይ ቁማሩና የፖለቲካ ሸፍጡ ይግባህ፡፤ ምንም ቀን አታባክን፡፡ ከውጭ ለሚነዙ ማስፈራሪያወች አንተ ጆሮ የለህም፡፤ እነርሱ ከማንነትህ አይልጡምና በዛሬውም በነገውም ህይወትህ መፍረድም አይችሉም፡፡አሁኑኑ በያለህበትእምቢበልና ተነሳ፡፡አብይ ሆይ፦ተነቅቶብሀል፡፡ በቃ!! ከእንግዲህ በአንተ ልፍለፋ የሚታለል አይኖርም፡፡ አዛዦችህም ከተጠቀሙብህ በኋላ እንደአገዳ መጥጠው ሲጥሉህ ያኔ ትረዳዋላህ፡፡ ህዝቤ ሆይ በራስህ ተማምነህ ተነሳ፤ አማራዬ ሆይ፦ ከኤርትራ ጋር ስትራቴጅክ ቁርኝት ፍጠርና ትጥቅህንና ስልጠናህን አጠናክረህ በተፈጥሮ በታደልከው ጀግንነትና በለመድከው ወኔ ጠላቶችህን ድባቅ ምታቸው፡፡ ታዲያ ያኔ ይህ እንደሚሆን አውቀን እኛም አይበልናንዶ ብለን ነበር እንላለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ይህ ፎቶግራፍ ብዙ ይናገራል (መሳይ መኮነን)

Next Story

የዐማራዉ ህዝብ እምነቶች

Go toTop