እጀታ! – በላይነህ አባተ

June 29, 2021

በሰዶም ኃጥያት ተጠምቀህ በይሁዳ እጆች ተጣመህ፣
ግንድ ቅርንጫፍ በመክዳት ተምሳር ቅርቃር ተሽጠህ፣
ስንቱን ቀጥ ያለ የዛፍ ዘር ቆርጦ በመጣል ያስፈጀህ፣
ያለፈው አልበቃ ብሎ ዛሬም ተፋሶች ተጣበክ፡፡

ስለት ባናትህ ሰክተህ ጫካና ዱሩን ጨፍጭፈህ፣
በውስጥ የሚኖሩትን አንበሶች ለጥቃት ጉዳት አጋልጠህ፣
በሜዳ አህያ ከርከሮ አገሩን ምድሩን አስወረርክ፡፡

በራስህ መንፈስ አታዝዝ አትጓዝ በገዛ እግሮችህ፣
ጅራትህን ተእጆች ወትፈህ ኩንቢህን ተምሳር ቅርቃር ቀርቅረህ፣
ዛሬም የዛፎችን ዘር ልታስፈጅ እንደ ትል ትወራጫለህ፡፡

እንደ አሽከር ሁሌ መታዘዝ የሎሌ ኑሮ ሳይቀፍህ፣
ዘርህ ተቆርጦ ማለቁ ተምድር መጥፋት ሳይቆጪህ፣
ትቢያ አመድ ሆነህ ታርፋለህ ተምድጃ ተእሳት ተጥለህ፣
የማታ ማታ ምሳሩ ገዝግዞ ቅልጥም አድርጎ ሲሰብርህ፣
ስኳር ላሹን ሰው ጠይቀው ይኸንን መልዕክት ታላመንክ፡፡

በተረገመው ተፈጥሮህ ባልተባረከው ምግባርህ፣
እንደ ሳጥናኤል ይሁዳ ስለት ብዕሮች ሲወጉህ፣
ታሪክ በመዛግብቱ ትውልድ በቅየው ሲወቅስህ፣
ምድር ተምድጃ ስጠብስህ ሰማይ ሲኦል ውስጥ ሲያነድህ፣
ጠማማው እንጨት እጀታ እስከ ዘላለም ይወሳል ክህደትህ፣
ተመልከት የአምስቱን ዘመን ባንዳዎች ቀፋፊ ታሪክ ታላመንክ፡፡

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የአማራ ክልል ልዩ ሀይል እና የኤርትራ ሰራዊት ድንበራቸውን ዘግተው ፤ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ቆመዋል !

Next Story

“በእኛ እና በመላ የአማራ ህዝብ መቃብር ላይ ካልሆነ ዳግም “ተከዜን” የሚሻገር አንዳች የትህነግ አሻባሪ ቡድን አይኖርም!” ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ

Latest from Same Tags

እምቢ በል! (በላይነህ አባተ)

ለሰላሳ ዓመታት ያየኸው ሰቆቃ፣ እስከ ዘላለሙ ዳግም እንዳይመጣ፣ እንደ ድር አብረህ አምቢ በል አማራ! የፈጠሙብህ ግፍ ቢሰፈር ቢቆጠር፣ እንኳን ቆሞ ኻጅን ሙትን ያሸፍታል፡፡ መታገስ
Go toTop

Don't Miss